Thursday, 2 November 2017

ግጥም


ግጥም፦ በዚህ አምድ ሥር ንባብን የሚያነሱና የሚያበረታቱ ግጥሞችን ምንለቅበት አምድ ነው፡፡

**ራሴን ላጠና**
አንባቢ አዋቂ ነው
ማንበብ ሰው ያደርጋል
ሲባል ሰማሁና መጽሐፉን ብገልጠው
የሰው መሠረቱ
የኑሮ ብልሃቱ ራሱን ማወቅ ነው
ሲለኝ እያብራራ
መጽሐፉን ዘግቼው ሙከራ ጀመርኩኝ
ራሴን ላጠና …….
ራሴን ሳነበው
አንቀፅም ምዕራፍም
መግቢያም መደምደሚያም
መውጫ ገጽ የሌለው
የምኞት ጋጋታ የኑሮ ሁካታ
ትልቅ ጎተራ ነው
ከዚህ ሁሉ መሀል
ለማን ነኝ?  ጥያቄ
ለራሴ ከራሴ መልሱን ስላጣሁት
የከፈትኩትን ራስ መልሼ ዘጋሁት

ከ *ልዑል ኃይሌ*

 

No comments:

Post a Comment