የንባብ ዜና፦ ስለ መጽሐፍ ሽያጭ፣ ንባብ ነክ መርሐ ግብሮችና የውይይት ግብዣዎችን ለአንባቢዎች መረጃ የሚተላለፍበት ነው፡፡
በዚህ ሳምንት አዳዲስ የመጻሕፍት በረከቶች
በዳዊት ደስታ ማንበብ ሙሉ ሰው ያደርጋል፡፡
1.
የአዳም
ረታ ‹‹አፍ›› አዲስ ረዥም ልብ ወለድ መጽሐፍ ለአንባቢያን አቅርቦል፡፡ መጽሐፉ ማክሰኞ 11 ሰዐት በብሔራዊ ቴአትር ይመረቃል፡፡
254 ገጾች የተቀነበበ ነው፡፡ ዋጋው 80 ብር ለገበያ ቀርቦል፡፡
2.
የዝነኛው
ደራሲ ጃክ ሂግኒስ ‹‹ድሪክ ዊዝ ዴቭል›› በተርጎሚ መልዓከ ተሰማ ‹‹ሰዎቹ›› በሚል ርዕስ ወደ አማርኛ ተመልሶ ለንባብ በቃ፡፡
216 ገጽ ተቀንብቦ በ61 ብር እየተሸጠ ነው፡፡
3.
‹‹ከዕለታት
አንድ ቀን›› የግጥም መጽሐፍ በሳምሶን የተዘጋጀ ሲሆን መጽሐፉ በ91 ገጾች 60 ግጥሞችን ይዞ በ 50 ብር እየተሸጠ ይገኛል፡፡
4.
‹‹ምሳሌያዊ
አነጋገር›› ሥነ ፍቺያዊ ፋይዳና አንድምታ መጽሐፍ በመምህርት ደራሲና ጋዜጠኛ ወይንሸት በየነ የተዘጋጀ 261 ገጾች ይዞ በ91.25
እየተሸጠ ይገኛል፡፡
ማንበብ ሙሉ ሰው ያደርጋል፡፡
ምንጭ አዲስ አድማስ መጋቢት 8 ቀን 2010 ዓ.ም
በዚህ ሳምንት አዳዲስ የመጻሕፍት በረከቶች
በዳዊት ደስታ ማንበብ ሙሉ ሰው ያደርጋል፡፡
1.
‹‹ያልነጋው
ቀን›› በገበያ ላይ ዋለ፡፡ መጽሐፉ በሦስት ክፍሎች የተከፈለ ነው፡፡ ‹‹ዘማን››፣ ‹‹ሶላና›› እና ‹‹ሲፋኒ-‹‹የሰላም ከተማ››
በሚሉ ርዕሶች፡፡ በ167 ገፆች ተመጥኖ የቀረበው ‹‹ያልነጋው ቀን›› ለአገር ውስጥ በ60 ብር ለውጭ አገራት በ20 ዶላር ለገበያ
ቀርቧል፡፡
2.
‹‹ማራ››
ልብ ወለድ መጽሐፍ ነገ ይመረቃል፡፡ የደራሲ ሰናይት ፍቃዴ ‹‹ማራ›› የተሰኘ ረዥም ልብ ወለድ መጽሐፍ በቅርስና ጥናት ጥበቃ ባለሥልጣን
አዳራሽ፤ የሥነጽሑፍ ባለሙያዎችና ተጋባዥ እንግዶች በተገኙበት ይመረቃል፡፡
ማንበብ ሙሉ ሰው ያደርጋል፡፡
ምንጭ አዲስ አድማስ ጋዜጣ፣ መጋቢት 15 ቀን 2010 ዓ.ም
በዚህ ሳምንት አዳዲስ የመጻሕፍት በረከቶች
በዳዊት ደስታ ማንበብ ሙሉ ሰው ያደርጋል፡፡
1. ‹‹Empire
and Revolution in Ethiopia›› በ345 ገጽ የተቀነበበው መጽሐፍ በ142 ብር በ20 ዶላርና በ15 ዩኬ ለገበያ ቀርቦል፡፡
2. ‹‹ነጻነትን
ፍለጋ››በ183 ገጽ የተቀነበበው መጽሐፍ በ91 ብር ከ60 ሳንቲም ለገበያ ቀርቧል፡፡
3. ‹‹ክልከላ››
ልብወለድ መጽሐፍ በደራሲ ዮርዳኖስ ሽፈራው የተዘጋጀ ሲሆን በ293 ገጽ ተቀንብቦ የቀረበ ሲሆን በ120 ብር ለአንባብያን ቀርቧል፡፡
ማንበብ ሙሉ ሰው ያደርጋል፡፡
ምንጭ፦
አዲስ አድማስ ጋዜጣ፣ መጋቢት 22 ቀን 2010 ዓ.ም
በዚህ ሳምንት አዳዲስ የመጻሕፍት በረከቶች
በዳዊት ደስታ ማንበብ ሙሉ ሰው ያደርጋል፡፡
1. ‹‹መንግሥትና የግለሰብ ነፃነት››
‹‹መንግሥትና የግለሰብ ነፃነት›› መጽሐፍ በገበያ
ላይ ዋለ፡፡ በደራሲ መካሻ አበራ የተፃፈው ‹‹መንግሥትና የግለሰብ ነፃነት›› የብአዴን ጽ/ቤት ኃላፊ በሆኑት አቶ አለምነው መኮንን
የተፃፈው ‹‹ፖለቲካ፣ ኢኮኖሚና የኢትዮጵያ ህዳሴ›› ለተሰኘው መጽሐፍ ምላሽ የሚሠጥ ነው ተብሏል፡፡ በአምስት ዋና ዋና ምዕራፎች
የተከፋፈለው መጽሐፍ በሪበራል ዴሞክራሲና ገበያ አክራሪነት፣ በምዕራባውያን የገበያ አክራሪነትና ሊበራል ዲሞክራሲ የቀረበውን ትችት
ዙርያ የሚያጠነጥን ነው፡፡ በ240 ገፅ የተመጠነው መጽሐፍ በ65 ብር እየተሸጠ ነው፡፡
2. ‹‹ገለዓድ የፍቅር ተራራ››
በደራሲ አለምነህ
እንግዳው የተፃፈው ወጥ ልብወለድ የሆነው ‹‹ገለዓድ የፍቅር ተራራ›› መጽሐፍ የሰሞን ጎዝ (የቅዳሴ) ትምህርት ለመማር ከሩቅ ቦታ
ወደ ጎንደር በለሳ ቃላይ መድኃኔዓለም ጥንታዊት ቤተክርስቲያን የሄደ የአንድ ወጣት የትምህርት እና የፍቅር ታሪክ የሚያስቃኝ መጽሐፍ
ነው፡፡ በ133 ገጽ የተቀነበበው መጽሐፍ በ60 ብር ለገበያ ቀርቦል፡፡
3. ‹‹ህይወት ምርጫ ነው››
በዶክተር በላይ ደርዛ ‹‹ህይወት ምርጫ ነው››
የተሰኘ መጽሐፍ ነገ ከረፋዱ 4፡00 ጀምሮ በብሔራዊ ቤተ መጻሕፍትና ቤተ መዛግብት ኤጀንሲ አዳራሽ ይመረቃል፡፡
ማንበብ ሙሉ ሰው ያደርጋል፡፡
ምንጭ፦
አዲስ አድማስ ጋዜጣ፣ ሚያዝያ 13 ቀን 2010 ዓ.ም
በዚህ ሳምንት አዳዲስ የመጻሕፍት በረከቶች
በዳዊት ደስታ ማንበብ ሙሉ ሰው ያደርጋል፡፡
1. ‹‹ያላረፉ ነፍሶች››
የደራሲ ቆንጅት ብርሃን 2ኛ ሥራ የሆነው
‹‹ያላረፉ ነፍሶች›› ረጅም ልብወለድ መጽሐፍ ለንባብ በቃ፡፡ በ398 ገፅ የተቀነበበው መጽሐፍ በ182 ብር ከ50 ሳንቲም ለገበያ
ቀርቦል፡፡
2. ‹‹ጎደኝነት››
በብስራ ጴጥሮስ ዩሣ የተዘጋጀው ‹‹ጎደኝነት
እና ሌሎች መሳጭ ታሪኮች›› የአጫጭር ታሪኮችና ግጥሞች ስብስብ መጽሐፍ ከትናንት በስቲያ ጀምሮ በገበያ ላይ ዋለ፡፡ በ125 ገጾች
የተቀነበበው መጽሐፍ በመልካም ሥነ-ምግባር እና በባህሪ ተሃድሶ ዙርያ የሚያተኩር 72 አጫጭር መሳጭ ታሪኮችና 13 ግጥሞችን ያካተተ
ነው፡፡ ዋጋው 71.50 ብር እየተሸጠ ነው፡፡
3. በ‹‹ተመስገን
ገብሬ ሕይወቱና ስራዎቹ›› መጽሐፍ ላይ ነገ ውይይት ይካሄዳል፡፡
ሚዩዚክ ሜይዴይ ከኢትዮጵስ ኮሌጅ ጋር በመተባበር
ነገ ከቀኑ 8፡00 ጀምሮ በብሔራዊ ቤተ-መዛግብትና ቤተ-መጻሕፍት ኤጄንሲ አዳራሽ ውይይት ይደረጋል፡፡ በእለቱ ለውይይቱ የመነሻ
ሃሰብ የሚያቀርቡት የአሀዱ ኤፍኤም ራዲዮ ሥራ አስኪያጅ፣ ደራሲና ጋዜጠኛ አቶ ጥበቡ በለጠ ሲሆኑ በውይይቱ እንድንገኝ ተጋብዘናል፡፡
ማንበብ ሙሉ ሰው ያደርጋል፡፡
ምንጭ፦
አዲስ አድማስ ጋዜጣ፣ ሚያዝያ 20 ቀን 2010 ዓ.ም
በዚህ ሳምንት አዳዲስ የመጻሕፍት በረከቶች
በዳዊት ደስታ ማንበብ ሙሉ ሰው ያደርጋል፡፡
1. ‹‹ኃይሌ ፊዳ እና የግሌ ትዝታ››
በዶ/ር አማረ
ተግባሩ የተጻፈው ‹‹‹‹ኃይሌ ፊዳ እና የግሌ ትዝታ›› የተሰኘ መጽሐፍ ለንባብ በቃ፡፡ መጽሐፉ በ1960ዎቹ መጨረሻ በዋናነት በአውሮፓ
የኢትዮጵያ ተማሪዎች ንቅናቄ እንዲሁም የመኢሶን መሪ በነበረው ኃይሌ ፊዳ ህይወት፤ ፖለቲካዊ ሚና እንዲሁም አጠቃላይ አብዮታዊ እንቅስቃሴ
የሚያስቃኝ መጽሐፍ ነው፡፡ መጽሐፉ 236 ገጾች የተቀነበበው በ111 ብር ከ50 ሳንቲም በገበያ ላይ ውሏል፡፡
2. ‹‹የኢንተርፕሪነርሽፕ ሀሁ››
በዶ/ር አቡሽ
አያሌውና እንድርያስ አራጋው የተጻፈው ‹‹የኢንተርፕሪነርሽፕ ሀሁ›› መጽሐፍ ‹‹የራስህን ቢዝነስ ለመጀመር አሁኑኑ ተነስ›› በሚል
ከንግድ ሀሳብ ፈጠራ እስከ ንግድ ሀሳብ እቅድ አነዳደፍ ድረስ በተግባር የተዋቀረ ትምህርት የሚሰጥ መጽሐፍ ነው፡፡ በ330 ገጾች
የተቀነበበው መጽሐፍ በ175 ብር በገበያ ውሏል፡፡
ማንበብ ሙሉ ሰው ያደርጋል፡፡
ምንጭ፦
አዲስ አድማስ ጋዜጣ፣ ሚያዝያ 27 ቀን 2010 ዓ.ም
በዚህ ሳምንት አዳዲስ የመጻሕፍት በረከቶች
በዳዊት ደስታ ማንበብ ሙሉ ሰው ያደርጋል፡፡
በህክምና
ባለሙያው ቸርነት ገብረ ክርስቶስ የተፃፈው በህክምና ላይ የሚያጠነጥን “ዲባቶ” የተሰኘ መፅሐፍ ለንባብ በቃ፡፡ መፅሐፉ በዋናነት በህክምናው አለም ያሉ የአካሚና የታካሚ እውነቶችን በስነ ፅሑፍ ለዛ እያዋዛ እውቀትና ግንዛቤ የሚያስጨብጥ ነው ተብሏል፡፡ በ371 ገፆች የተቀነበበው መፅሐፉ በ160 ብር እና በ20 ዶላር…
2. “የ21ኛው ክ/ዘመን መሳፍንትና ኢትዮጵያን እንደ ሀገር የማስቀጠል ፈተና” ዛሬ ይመረቃል
የእውቁ
ፖለቲከኛና መሐንዲስ ኢ/ር ዘለቀ ረዲ፣ “የ21ኛው ክ/ዘመን መሳፍንትና ኢትዮጵያን እንደ ሀገር የማስቀጠል ፈተና” የተሰኘው መፅሐፍ የፊታችን ሰኞ ከቀኑ 11፡00 ጀምሮ በዋቢ ሸበሌ ሆቴል ይመረቃል፡፡ በምርቃት ስነ ስርዓቱ ላይ የመፅሐፉ ዳሰሳ (review)፣ እንዲሁም ከመፅሐፉ የተመረጡ ክፍሎች የሚቀርቡ ሲሆን ውይይትም ይደረጋል ተብሏል፡፡
ምንጭ፦
አዲስ አድማስ ጋዜጣ፣ ግንቦት 4 ቀን 2010 ዓ.ም
በዚህ ሳምንት አዳዲስ የመጻሕፍት በረከቶች
በዳዊት ደስታ ማንበብ ሙሉ ሰው ያደርጋል፡፡
“የአመራር ሳይንስና ጥበብ” መፅሀፍ ገበያ ላይ ዋለ
በኮሎኔል ፈቃደ ገብረየሱስ የተሰናዳውና በአመራር ሳይንስና ጥበብ ላይ ሰፊ ትንታኔ የሚሰጠው “የአመራር ሳይንስና ጥበብ” መፅፍ ገበያ ላይ ዋለ፡፡ “የሁሉን ነገር መውደቅም ሆነ መነሳት የሚወስነው አመራር ነው” የሚለው የጆን ማክስዌልን አመራር ተንተርሶና የተለያዩ ውጤታማ ተሞክሮ ያላቸውን አመራሮች ልምድ ቀምሮ የተዘጋጀው መፅሀፉ በተለያዩ የሙያ ዘርፎች አመራር ያለውን ጉልህ ሚና በማስተማር ሰዎች ቢዝነሳቸውን፣ ቤተሰባቸውን እና ተቋማትን እንዴት መምራት እንደሚችሉ ጥበብን ያላብሳል ተብሏል በ704 ገፅ የተቀነበበው መፅሀፉ በ300 ብር ለገበያ ቀርቧል ደራሲው ከዚህ ቀደም “ስትራቴጂ” የተሰኘው የቢዝነስ ስትራቴጂን እውቀት የሚያስጨብጥ መፅሀፍ ለንባብ ማብቃታቸው ይታወሳል፡፡
“ደቦ” ለንባብ በቃ
ከተለያየ
የሙያ ዘርፍ የተውጣጡ 60 ነባርና አዳዲስ ፀሐፍት የተሳተፉበት “ደቦ 60 ደራሲያን” የተሰኘ መፅሀፍ ለንባብ በቃ፡፡ በዚህ መፅሀፍ ላይ ደራሲያን፣ ገጣሚያን መምህራን የሙዚቃ ባለሙያዎች፣ ተዋንያን፣ ጋዜጠኞች እና በተለያየ የሙያ ዘርፍ የተሰማሩ ግለሰቦች ያበረከቷቸው ወጎች፣ አርቲክሎች ግጥሞች፣ የፖለቲካ ትንታኔዎችና መሰል ፅሁፎች ተካትተውበታል፡፡ በዛጎል መፃህፍት ተዘጋጅቶ በደራሲ እንዳለ ጌታ ከበደ አርትኦቱ የተሰራለት መፅሀፉ በ516 ገፅ ተቀንብቦ በ170 ብር ለገበያ ቀርቧል፡፡
ምንጭ፦
አዲስ አድማስ ጋዜጣ
በዚህ ሳምንት አዳዲስ የመጻሕፍት በረከቶች
በዳዊት ደስታ ማንበብ ሙሉ ሰው ያደርጋል፡፡
“የልብ ቃጠሎ” እና “ንውዘት” ነገ ይመረቃሉ
በገጣሚና ደራሲ አበበ ካብ ይመር የተፃፉት “ንውዘት” የግጥም መፅሐፍና “የልብ ቃጠሎ” የአጫጭር ልቦለዶች ሥብስብ ነገ ከቀኑ 3፡30 ጀምሮ በዋቢ ሸበሌ ሆቴል አዳራሽ ይመረቃሉ፡፡ ንውዘት የግጥም መፅሐፍ በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ የሚያጠነጥኑ ከ80 በላይ ግጥሞችን የያዘ ሲሆን በ112 ገፅ ተቀንብቦ በ50 ብር ለገበያ ቀርቧል፡፡
የልብ ቃጠሎ የተሰኘውም መፅሃፋቸው በማህበራዊ ጉዳዮች ላይ የሚያጠነጥኑ 12 ያህል አጫጭር ልቦለዶችን የያዘ ሲሆን በ134 ገፅ ተቀንብቦ በ60 ብር ለገበያ ቀርቧል፡፡ በዕለቱ ተ/ፕሮፌሰር ዘሪሁን አስፋውና ረ/ፕሮፌሰር ደረጀ ገብሬ በመፅሐፍቱ ላይ ዳሰሳ እንደሚያቀርቡና አንጋፋና ወጣት ፀሐፍት ስራዎቻቸውን እንደሚያቀርቡ ለማወቅ ተችሏል፡፡
“ግርምተ ሳይቴክ” መፅሐፍ ተመረቀ
በኢቢኤስ ቴሌቪዥን “ቴክ ቶክ” በተሰኘው ሾው አስገራሚ የቴክኖሎጂ ውጤቶችን በማስተዋወቅና በመተንተን የሚታወቀው የሰለሞን ካሳ “ግርምተ ሳይቴክ” መፅሐፍ ከትንት በስቲያ ከምሽቱ 12፡00 ጀምሮ በሸራተን ሆቴል ላሊበላ አዳራሽ ተመረቀ፡፡ መፅሐፉ ለኢትዮጵያውን እንዲያገለግል በአማርኛ የተፃፈ ሲሆን፤ የምረቃው ሥነ ስርዓት በሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የተዘጋጀውን የአይሲቲ ኤክስፖ ኢትዮጵያ
2010 የአይሲቲ ሳምንት ምክንያት በማድረግ የተዘጋጀ እንደሆነና በምረቃ ሥነ ስርዓቱ ላይ የሚኒስትሩ የስራ ኃላፊዎች፣ በዘርፉ የተሰማሩ ባለሙያዎችና ተጋባዥ እንግዶች እንደተገኙም ታውቋል፡፡
ምንጭ፦
አዲስ አድማስ ጋዜጣ
በዚህ ሳምንት አዳዲስ የመጻሕፍት በረከቶች
በዳዊት ደስታ ማንበብ ሙሉ ሰው ያደርጋል፡፡
በ“ዕድል ፈንታ” ላይ ውይይት ይካሄዳል
ሚዩዚክ ሜይዴይ ኢትዮጵያ ከኢትዮጵስ ኮሌጅ ጋር በመተባበር፣ ነገ ከቀኑ 8፡00 ጀምሮ በስነ - ፅሑፍ የኖቤል ሽልማት አሸናፊ በሆነው ጀርመናዊው ደራሲ ሔርማን ካርልሔስ “ናርሲስ ኤንድ ጎልድመንድ” በሚል በተፃፈውና በተርጓሚ ሰላምይሁን ኢዶሳ “ዕድል ፈንታ” በሚል ወደ አማርኛ በተመለሰው መፅሐፍ ላይ በብሔራዊ ቤተ መፃሕፍትና ቤተ - መዛግብት ኤጀንሲ አዳራሽ ውይይት ያካሂዳል፡፡
ለውይይቱ የመነሻ ሀሳብ የሚያቀርበው “የማዕበል ጥንስስ” እና “ሰልስቱ ጣዖታት” መፃህፍት ደራሲ ያዕቆብ ብርሃኑ ሲሆን መድረኩን የሚመራው የቋንቋ መምህርና የታሪክ ባለሙያ በሆነው ሰለሞን ተሰማ ጂ. እንደሆነ አዘጋጁ ገልፆ፤ በውይይቱ ላይ ፍላጎት ያለው እንዲሳተፍ ጥሪ ቀርቧል፡፡
ለውይይቱ የመነሻ ሀሳብ የሚያቀርበው “የማዕበል ጥንስስ” እና “ሰልስቱ ጣዖታት” መፃህፍት ደራሲ ያዕቆብ ብርሃኑ ሲሆን መድረኩን የሚመራው የቋንቋ መምህርና የታሪክ ባለሙያ በሆነው ሰለሞን ተሰማ ጂ. እንደሆነ አዘጋጁ ገልፆ፤ በውይይቱ ላይ ፍላጎት ያለው እንዲሳተፍ ጥሪ ቀርቧል፡፡
ማንበብ ሙሉ ሰው ያደርጋል፡፡
በዚህ ሳምንት አዳዲስ የመጻሕፍት በረከቶች
በዳዊት ደስታ ማንበብ ሙሉ ሰው ያደርጋል፡፡
የሕይወት እምሻው “ፍቅፋቂ” ሐሙስ ተመረቀ
“ፍቅፋቂ” በሚል ርዕስ የተዘጋጀው የሕይወት እምሻው ሁለተኛ መጽሐፍ ከትላንት በስቲያ ሐሙስ፣ ሐምሌ 5 ቀን
2010 ዓ.ም. በዋቢ ሸበሌ ሆቴል ተመርቋል፡፡ የደራሲዋ ሁለተኛ ሥራ የሆነው ይህ የልቦለዶችና የወጎች ስብስብ መጽሐፍ፤ በ220 ገጾች ላይ የተዘራ ሲሆን 38 ዋና ዋና እና 20
መሻገሪያ ትረካዎችን ያካትታል፡፡
ደራሲዋ እንደ በኩር ሥራዋ ሁሉ በአዲሱ መጽሐፏ ውስጥ በሚገኙ ትረካዎችም የኢትዮጵያዊያንን ፍቅር፣ ባህል፣ ፖለቲካ፣ የዕለት ተዕለት ሕይወት እያነሳች በቅርበትና በኪናዊ ለዛ ትበልታለች፤ እንደ አስገድዶ መድፈርና ድንግልናን የመሳሰሉ ጉዳዮችንም ተጠየቅ ውስጥ ትከታለች፡፡
ሕይወት ከደራሲነትም ባሻገር “ነቆራ እና ሌሎችም ወጎች ከሕይወት እምሻው ጋር” የተሰኘ ከመቶ ሠላሳ ሺህ በላይ ተከታዮች ያሉት የፌስቡክ ገጿ ላይም በቋሚነት በመጻፍ ትታወቃለች፡፡ በመጽሐፍት መልኩ መገለጥን ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ከመጻፍ ጋር በማነጻጸር “ሁለቱ ፍጹም የተለያዩ ሂደቶች ናቸው” የምትለው ደራሲዋ፤ “ፌስቡክ ላይ መጻፍ ፍጥነት አለው፤ ስሜታዊና ቅጽበታዊም ነው፡፡ በአብዛኛው በጥሞና ከማሰላሰልና የፈጠራ ችሎታን ከመጠቀም የሚያቅብ ድርጊትም ሊሆን ይችላል፡፡ በአንጻሩ መጽሐፍ ማዘጋጀት ጊዜ ይወስዳል፣ ከፍተኛ ጥንቃቄና ተደራራቢ የአርትዖት ደረጃዎችንም ያልፋል” ትላለች፡፡
ከሦስት ዓመታት በፊት ባሳተመችው የመጀመሪያ መጽሐፏ “ባርቾ” የወጎችና የልቦለዶች ስብስብ፣ ኢትዮጵያዊያን ሊነጋገሩባቸው የማይደፍሯቸውን “አይነኬ” ጉዳዮች እያነሳች በዋዛና በቁምነገር በመተረኳ የበርካታ አንባቢዎች ልብ ውስጥ እንድትገባ አድርጓታል፡፡
ደራሲዋ ለወደፊትስ እጅሽ ከምን ለሚሏት ወዳጆቿ፤ “አንድ ረጅም ልቦለድ እየጻፍኩ ነው” ትላለች፡፡ “እኔ የምታወቀው ኳ! በሚያደርጉ በጣም አጫጭር ሥራዎች ስለሆነ ይሄ ከዚህ በፊት ያልታየሁበት ቀጠና ይሆናል፡፡ ከ‘ባርቾ’ እና ከ‘ፍቅፋቂ’ ጋር በይዘትና በቅርጽ የሚመሳሰል ሌላ ሦስተኛ መጽሐፍም አዘጋጃለሁ” ስትልም አክላለች፡፡

“ፍቅፋቂ” በሊትማን መጻሕፍት አከፋፋይነት ካለፈው ሐሙስ ጀምሮ በ92 ብር ዋጋ በገበያ ላይ ውሏል፡፡
ማንበብ ሙሉ ሰው ያደርጋል፡፡
በዚህ ሳምንት አዳዲስ የመጻሕፍት በረከቶች
በዳዊት ደስታ ማንበብ ሙሉ ሰው ያደርጋል፡፡
“መወልወያ አዟሪው እና ሌሎችም” ለንባብ በቃ
በደራሲ ሳምሶን ከፍያለው የተደረሱ አምስት አጫጭር ልቦለድ ታሪኮችን ያካተተው “መወልወያ አዟሪው እና ሌሎችም” መፅሐፍ ገበያ ላይ ዋለ፡፡ መፅሐፉ “ፍቅርና ንፋስ፣ “ጠርጣራው ደምሴ”፣ “ዣንጥላው ስር ሆነን”፣ “ልጅ‘ኮነሽ” እና “መወልወያ አዟሪው” የተሰኙ ከዕለት ተዕለት ህይወታችን ጋር የተቆራኙ ማህበራዊ ጉዳዮች የተዳሰሱባቸው ታሪኮች ተካትተውበታል፡፡
የደራሲው ሶስተኛ ስራ የሆነው ይሄው መፅሐፍ፤ በ140 ገፆች ተቀንብቦ፣ በ70 ብር ለገበያ የቀረበ ሲሆን ደራሲው ከዚህ ቀደም “እንባና ትውስታ” እና “ከእለታት አንድ ቀን” የተሰኙ የአጭር ልቦለድና የግጥም መፅሐፎችን ለንባብ ማብቃቱ አይዘነጋም፡፡
የደራሲው ሶስተኛ ስራ የሆነው ይሄው መፅሐፍ፤ በ140 ገፆች ተቀንብቦ፣ በ70 ብር ለገበያ የቀረበ ሲሆን ደራሲው ከዚህ ቀደም “እንባና ትውስታ” እና “ከእለታት አንድ ቀን” የተሰኙ የአጭር ልቦለድና የግጥም መፅሐፎችን ለንባብ ማብቃቱ አይዘነጋም፡፡
ምንጭ፦
አዲስ አድማስ ጋዜጣ
በዚህ ሳምንት አዳዲስ የመጻሕፍት በረከቶች
በዳዊት ደስታ ማንበብ ሙሉ ሰው ያደርጋል፡፡
የዳንኤል ክብረት “የአዲስ አበባ ውሾች”
“-- አሪፍ ውሻ ማለት ክፉ ውሻ ነው፣ እንደ ማለት ነው፡፡ አንተ ክፉ ውሻ ከሆንክ ለጌቶችህ አሪፍ ውሻ ነህ፡፡ ትናከስላቸዋለህ፣ ትጮህላቸዋለህ፣ መንገድ አላፊውን ታስደነብርላቸዋለህ፣ ታስፈራራላቸዋለህ። ለሌላው ክፉ ስትሆን ለጌቶችህ ምርጥ ውሻ ትሆናለህ። በኋላ ላይ ግን እዳው አንተ ላይ ይወድቃል፤ በመጨረሻ አንተው ትወረወራለህ፤ ለጅቦቹም ተላልፈህ ትሰጣለህ-”
ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ከላይ እንዳነበባችሁት ስለ “የአዲስ አበባ ውሾች” ያወጋናል- በአዲሱ መፅሐፉ። የአዲስ አበባ ውሾች ግን ተምሳሌታዊ ናቸው - ደራሲው የቀረፃቸው ሰውን እንዲወክሉለት ነው፡፡ ታሪኩ የፖለቲካና ማህበራዊ ስላቅ ሊባል ይችላል። ስለ ዘመኑ ሙሰኛ የመንግስት ባለሥልጣናት፣ ስለ ሞሳኝ ባለፀጎች፣ ስለ ዳያስፖራ ወዘተ … ከጭቁኑ የአዲሳቤ ነዋሪ ጋር እየተነፃፀረ ይተረክልናል - በማራኪ ቋንቋና በሚያዝናና አቀራረብ፡፡ በ253 ገፆች የተቀነበበው የዳንኤል ክብረት መፅሐፍ፤ በ100 ብር ለገበያ ቀርቧል፡፡
ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ከላይ እንዳነበባችሁት ስለ “የአዲስ አበባ ውሾች” ያወጋናል- በአዲሱ መፅሐፉ። የአዲስ አበባ ውሾች ግን ተምሳሌታዊ ናቸው - ደራሲው የቀረፃቸው ሰውን እንዲወክሉለት ነው፡፡ ታሪኩ የፖለቲካና ማህበራዊ ስላቅ ሊባል ይችላል። ስለ ዘመኑ ሙሰኛ የመንግስት ባለሥልጣናት፣ ስለ ሞሳኝ ባለፀጎች፣ ስለ ዳያስፖራ ወዘተ … ከጭቁኑ የአዲሳቤ ነዋሪ ጋር እየተነፃፀረ ይተረክልናል - በማራኪ ቋንቋና በሚያዝናና አቀራረብ፡፡ በ253 ገፆች የተቀነበበው የዳንኤል ክብረት መፅሐፍ፤ በ100 ብር ለገበያ ቀርቧል፡፡
በዚህ ሳምንት አዳዲስ የመጻሕፍት በረከቶች
በዳዊት ደስታ ማንበብ ሙሉ ሰው ያደርጋል፡፡
“ሌላ ዓለም” የአጫጭር ልቦለዶች መጽሐፍ
በተለያዩ ጭብጦች ላይ የሚያጠነጥኑ 18
አጫጭር ልቦለዶችን ያካተተው የደራሲ ዮናስ ብርሃኔ “ሌላ ዓለም” የተሰኘ መፅሐፍ ለንባብ ቀረበ፡፡ በ132 ገፆች የተቀነበበው መፅሐፉ፤ በ65 ብር ለገበያ ቀርቧል፡፡ ደራሲ ዮናስ ብርሃኔ ከዚህ ቀደም “አማሌሌ እና ሌሎችም” በተሰኘ መፅሐፍ ውስጥ ሁለት ወጎችንና ሁለት አጫጭር ልቦለድ ታሪኮችን በማዋጣት ለንባብ ያበቃ ሲሆን አዲስ አድማስን ጨምሮ በተለያዩ ጋዜጦችና መፅሔቶች ላይ በሚያቀርባቸው ፅሑፎች ይታወቃል፡፡
በዚህ ሳምንት አዳዲስ የመጻሕፍት በረከቶች
በዳዊት ደስታ ማንበብ ሙሉ ሰው ያደርጋል፡፡
“መቆያ 1” እና “እሪ በከንቱ” የግጥም መድበሎች
በገጣሚ መላዕከ ብርሃን አድማሱ የተፃፉና በበርካታ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ ከ110 በላይ ግጥሞችን ያካተተው “መቆያ 1” የግጥም መድበል በገበያ ላይ ዋለ፡፡ በ121 ገፆች የተመጠነው መፅሐፉ፤ በ100 ብር ለገበያ የቀረበ ሲሆን በቅርቡ እንደሚመረቅም ተነግሯል፡፡
በተመሳሳይ፤ በአዲስ አበባ በልማት ስም እየተነሱ ወደ ጥግ በሚገፉ ነዋሪዎችና በመዲናዋ መቆሸሽ ዙሪያ የሚያጠነጥኑ ከ80 በላይ ግጥሞችን የያዘው “እሪ በከንቱ” የተሰኘው የገጣሚ ዳንኤል ታረቀኝ የግጥም መድበል ሰሞኑን ለንባብ በቅቷል፡፡
የ“ሪፖርተር” ጋዜጠኛ ነአምን አሸናፊ በመፅሐፉ ጀርባ ላይ ባሰፈረው አስተያየት፤ “… በዚህ የግጥም መድበል ውስጥ ለአብነት ያህል “ጮኸብኝ ዝምታ”፣ “የኛ ቤት”፣ “ሽንትና አዲስ አበባ”፣ “ዝምታ መልስ ነው”፣ “ወዴት አለሽ ሞራል”፣ “ጉዞ ወደ ሁካታ” እና “የደም ውለታ” የተሰኙት ስነ ልቦናዊ፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ግጥሞች የገጣሚውን ጥልቅ ትዝብት ያንፀባርቃሉ፡፡” ብሏል፡፡ 84 ገፆች ያሉት መድበሉ፤ ዋጋው 46 ብር ከ90 ሳንቲም ነው፡፡
በተመሳሳይ፤ በአዲስ አበባ በልማት ስም እየተነሱ ወደ ጥግ በሚገፉ ነዋሪዎችና በመዲናዋ መቆሸሽ ዙሪያ የሚያጠነጥኑ ከ80 በላይ ግጥሞችን የያዘው “እሪ በከንቱ” የተሰኘው የገጣሚ ዳንኤል ታረቀኝ የግጥም መድበል ሰሞኑን ለንባብ በቅቷል፡፡
የ“ሪፖርተር” ጋዜጠኛ ነአምን አሸናፊ በመፅሐፉ ጀርባ ላይ ባሰፈረው አስተያየት፤ “… በዚህ የግጥም መድበል ውስጥ ለአብነት ያህል “ጮኸብኝ ዝምታ”፣ “የኛ ቤት”፣ “ሽንትና አዲስ አበባ”፣ “ዝምታ መልስ ነው”፣ “ወዴት አለሽ ሞራል”፣ “ጉዞ ወደ ሁካታ” እና “የደም ውለታ” የተሰኙት ስነ ልቦናዊ፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ግጥሞች የገጣሚውን ጥልቅ ትዝብት ያንፀባርቃሉ፡፡” ብሏል፡፡ 84 ገፆች ያሉት መድበሉ፤ ዋጋው 46 ብር ከ90 ሳንቲም ነው፡፡
በዚህ ሳምንት አዳዲስ የመጻሕፍት በረከቶች
በዳዊት ደስታ ማንበብ ሙሉ ሰው ያደርጋል፡፡
“ከትግል ትዝታዎቼ” መፅሐፍ
በአንጋፋው የህወሓት ታጋይና መስራች ግደይ ዘርአጽዮን የተፃፈው “ከግል ትዝታዎቼ” የተሰኘ መፅሐፍ ገበያ ላይ ውሏል፡፡ ታጋዩ ጸሃፊ፤ በሴረኞች ተቀጨ የሚሉትን የደደቢት አብዮት በስፋት በሚተረኩበት በዚህ መጽሐፋቸው፤ህወሓትን አስመልክቶ በጭፍን ጥላቻ ስለተፃፉ መፅሐፍትና በህወሓት ውስጥ ያልሰሩትን ሰሩ ብሎ ግለሰቦችን በማሞገስ ህዝቡ የአምልኮ ያህል እንዲቀበላቸው የተደረገበትን መንገድ ያጋልጣሉ፡፡ ስለ ድርጅቱ በመጠኑም ቢሆን በሚዛናዊነት የጻፉ ግለሰቦችን የሚጠቅሱት የህወኃት መሥራች፤ሁሉም ፀሐፍት ለአሁኑ መፅሐፋቸው መነሻ በመሆናቸው አመስግነዋል፡፡
ከድርጅቱ እስከለቀቁበት ጊዜ ድረስ በከፍተኛ የአመራር ቦታ ላይ እንደነበሩ በመግለፅም፤ ትክክለኛውን የህወሓትን መልክና ቁመና በትክክለኛው መንገድ ለማሳየት ጥረት ማድረጋቸውን ጠቁመዋል፡፡ የተለያዩ ሰነዶችንና ምስሎችን ጨምሮ በ261 ገፆች የተቀነበበው መፅሐፉ፤ በ200 ብር ለገበያ የቀረበ ሲሆን ክብሩ መፅሐፍት መደብር እያከፋፈለው መሆኑ ታውቋል፡፡
ከድርጅቱ እስከለቀቁበት ጊዜ ድረስ በከፍተኛ የአመራር ቦታ ላይ እንደነበሩ በመግለፅም፤ ትክክለኛውን የህወሓትን መልክና ቁመና በትክክለኛው መንገድ ለማሳየት ጥረት ማድረጋቸውን ጠቁመዋል፡፡ የተለያዩ ሰነዶችንና ምስሎችን ጨምሮ በ261 ገፆች የተቀነበበው መፅሐፉ፤ በ200 ብር ለገበያ የቀረበ ሲሆን ክብሩ መፅሐፍት መደብር እያከፋፈለው መሆኑ ታውቋል፡፡
ምንጭ፦
አዲስ አድማስ ጋዜጣ
በዚህ ሳምንት አዳዲስ የመጻሕፍት በረከቶች
በዳዊት ደስታ ማንበብ ሙሉ ሰው ያደርጋል፡፡
“ምስጢረ ፊደል” ለገበያ ቀረበ
ደራሲ፣
ጋዜጠኛና የባህል ተመራማሪ መምህር ካሕሳይ ገ/እግዚአብሔር ያዘጋጁት “ምስጢረ ፊደል ወትርጓሜሁ” (የፊደል ምስጢር ከእነ ትርጉሙ) የተሰኘ መፅሐፍ ሰሞኑን ለገበያ ቀረበ፡፡
“ምስጢረ ፊደል፤ የግዕዝ ቋንቋና ፊደል ለሀገራችን ሥነ ፅሁፍ ባህል፣ ትውፊትና ታሪክ መሰረትና ምንጭ ብቻ ሳይሆን የጥንታዊ ሥልጣኔያችን መሰረት … እንዲሁም የግዕዝ ፊደል የራሱ ትርጉምና ምስጢር ያለው መሆኑን የሚያሳይና በውስጡ ለጥናትና ምርምር መነሻ የሚሆኑ አዳዲስ መረጃዎችን ያካተተ ነው፡፡ ከሁሉም በላይ በትክክለኛ የሆሄያት አፃፃፍ መሰረት መፃፍ ለሚፈልጉ ፀሐፍት፣ ደራሲያን፣ ተማሪዎች በመረጃ ምንጭነት የሚያገለግል ጭምር ነው” ብለዋል ደራሲው - ስለ መፅሐፉ በላኩት አጭር ሃተታ፡፡ “ምስጢረ ፊደል” ለደራሲ ካሕሳይ ሰባተኛ መፅሐፋቸው ሲሆን ከዚህ ቀደም “የኃብር ብዕር መፅሐፍ” (ከ1ኛ መፅሐፍ እስከ 3ኛ መፅሐፍ)፣ “ምንኩሳን በኢትዮጵያ”፣ “ብፅዓን እነማን ናቸው” እና “ባህልና ክርስቲያናዊ ትውፊት በኢትዮጵያ” የሚሉ መፃህፍትን ለንባብ ማብቃታቸው ይታወሳል፡፡ በ292 ገፆች የተቀነበበው “ምሥጢረ ፊደል”፤ በ110 ብር ይሸጣል፡፡
ምንጭ፦
አዲስ አድማስ ጋዜጣ
በዚህ ሳምንት አዳዲስ የመጻሕፍት በረከቶች
በዳዊት ደስታ ማንበብ ሙሉ ሰው ያደርጋል፡፡
የቀድሞ የመንግሥት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ሚኒስትር ዴኤታ የነበሩትና በአሁኑ ወቅት የ”ኢሳት” ፖለቲካዊ ጉዳዮች ተንታኝና ፕሮግራም አዘጋጅ በሆኑት አቶ ኤርሚያስ ለገሰ የተጻፈው “ጥላሁን ያረፈ ቀን” የተሰኘ መጽሐፍ በሳምንቱ መገባደጃ ላይ ለአንባቢያን ቀርቧል፡፡
በ310 ገፆች የተቀነበበው መፅሐፉ፤ በ182 ብር ለገበያ የቀረበ ሲሆን ከመፅሐፉ ገቢ ግማሹ፣ ለበርካታ ዓመታት በእስር ለቆየው ፖለቲከኛ ክንፈ ሚካኤል ደበበ (አበበ ቀስቶ)፣ የህክምና ወጪ እንደሚውል ለማወቅ ተችሏል፡፡ ደራሲው የመፅሐፉን መታሰቢያነት ለክቡር ዶክተር አርቲስት ጥላሁን ገሰሰ አድርጓል፡፡ አቶ ኤርሚያስ ለገሰ፤ ከዚህ ቀደም “ባለቤት አልባ ከተማ” እና “የመለስ ልቃቂት” የተሰኙ አገራዊ የፖለቲካ ጉዳዮችን የሚዳስሱ መጻሕፍትን ለአንባቢያን ማድረሳቸው ይታወሳል፡፡

“ለኢትዮጵያ አንድነት የተከፈለ የደምና የአጥንት ዋጋ”
በደራሲ ደርቤ መንግስቱ የተፃፈውና በወቅቱ የአገሪቱ የለውጥ ሂደት ላይ የሚያጠነጥነው “ለኢትዮጵያ አንድነት የተከፈለ የደምና የአጥንት ዋጋ” የተሰኘ መጽሐፍ ሰሞኑን ለንባብ በቅቷል፡፡
መፅሐፉ ከ20 አመታት መለያየት በኋላ በወረደው ሰላም ዳግም ስለተገናኙት የኢትዮጵያና ኤርትራ ህዝቦች፣ ባልተፈፀመ ታሪክ ጥላቻን በመንዛት፣ በአማራና ኦሮሞ ወንድማማች ህዝቦች ላይ ተፈጥሮ ስለነበረው ግጭትና ግጭቱ ስለተፈታበት መንገድ እንዲሁም ለአገር አንድነት ሲባል ስለተከፈለ መስዋዕትነት በጥልቀት ይዳስሳል። ለአገራቸው ደምና አጥንት የከፈሉ ጀግኖችን ክብርና ሞገስ የሚሰጠው መጽሐፉ፤አንዳንዶቹን በፎቶግራፍ ጭምር በማስደገፍ ለመዘከር ይሞክራል፡፡ መጽሐፉ በ291 ገጾች የተቀነበበ ሲሆን በ160 ብር ይሸጣል፡፡

በደራሲ አበበ ኃብተሥላሴ የተጻፈውና አዲሱ የለውጥ ጉዞን አቅጣጫ የሚያመላክተው “ኢትዮጵያዊነት፣ ኢኮኖሚያዊ ልማትና እንቆቅልሾቹ” የተሰኘ መፅሐፍ ገበያ ላይ ዋለ፡፡
መፅሐፉን ለመፃፍ ያነሳሳቸው፣ በምርጫ 97 የተፈፀመው የህዝብ “የሚመራኝን እመርጣለሁ” እና የአገዛዙ የድምፅ መስረቅና የህዝብን ድል የመቀልበስ ድርጊት እንደሆነ በመግቢያቸው የጠቆሙት ደራሲው፤ በወቅቱ ስለ ህወሓት/ኢህአዴግ ልማታዊ መንግስትነት የቀረቡ ፅሁፎች ህዝብን የተሳሳተ እሳቤ እንዲይዝ ያደረገ በመሆኑ፣ ይህንን የተሳሳተ እሳቤ ለማስተካከልና በዘርፉ የተሰማሩ ባለሙያዎች፣ ተጨማሪ ፅሁፍ እንዲያቀርቡ ለማነሳሳት መሆኑን ያስረዳሉ፡፡ ስለ ስልጣኔ አካሄድ በኢትዮጵያ፣ ስለ ኢኮኖሚያዊ ዕድገትና ኢኮኖሚያዊ ልማት፣ ስለ ልማታዊ መንግስትና ምንነትና ተያያዥ ጉዳዮች በስፋት የሚዳስሰው መፅሐፉ፤ በአራት ክፍሎች፣ በሰባት ምዕራፎችና በ216 ገፆች የተቀነበበ ሲሆን በ100 ብር እና በ20 ዶላር ለገበያ ቀርቧል፡፡ መጽሐፉን ክብሩ መፅሐፍት መደብር እንደሚያከፋፍለው ለማወቅ ተችሏል፡፡
መፅሐፉን ለመፃፍ ያነሳሳቸው፣ በምርጫ 97 የተፈፀመው የህዝብ “የሚመራኝን እመርጣለሁ” እና የአገዛዙ የድምፅ መስረቅና የህዝብን ድል የመቀልበስ ድርጊት እንደሆነ በመግቢያቸው የጠቆሙት ደራሲው፤ በወቅቱ ስለ ህወሓት/ኢህአዴግ ልማታዊ መንግስትነት የቀረቡ ፅሁፎች ህዝብን የተሳሳተ እሳቤ እንዲይዝ ያደረገ በመሆኑ፣ ይህንን የተሳሳተ እሳቤ ለማስተካከልና በዘርፉ የተሰማሩ ባለሙያዎች፣ ተጨማሪ ፅሁፍ እንዲያቀርቡ ለማነሳሳት መሆኑን ያስረዳሉ፡፡ ስለ ስልጣኔ አካሄድ በኢትዮጵያ፣ ስለ ኢኮኖሚያዊ ዕድገትና ኢኮኖሚያዊ ልማት፣ ስለ ልማታዊ መንግስትና ምንነትና ተያያዥ ጉዳዮች በስፋት የሚዳስሰው መፅሐፉ፤ በአራት ክፍሎች፣ በሰባት ምዕራፎችና በ216 ገፆች የተቀነበበ ሲሆን በ100 ብር እና በ20 ዶላር ለገበያ ቀርቧል፡፡ መጽሐፉን ክብሩ መፅሐፍት መደብር እንደሚያከፋፍለው ለማወቅ ተችሏል፡፡
ማንበብ ሙሉ ሰው ያደርጋል፡፡
ምንጭ፦
አዲስ አድማስ ጋዜጣ
በዚህ ሳምንት አዳዲስ የመጻሕፍት በረከቶች
በዳዊት ደስታ ማንበብ ሙሉ ሰው ያደርጋል፡፡
“የጨለማው መጋረጃ ሲቀደድ” ነገ ይመረቃል
በደራሲ ሳህሉ አድማሱ የተዘጋጀው “የጨለማው መጋረጃ ሲቀደድ” የተሰኘ መፅሐፍ ነገ ከቀኑ 8፡00 ጀምሮ ቤሊየር አካባቢ በሚገኘው አዲስ ቪው ኢንተርናሽናል ሆቴል ይመረቃል፡፡ የምረቃ ሥነ ስርዓቱ በተለያዩ ኪነ ጥበባዊ ዝግጅቶች የሚታጀብ ሲሆን መፅሐፉም ይገመገማል ተብሏል፡፡መፅሐፉ ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ወደ ስልጣን ከመጡ ወዲህ በሳቸው አመራር የተመዘገቡ ዋና ዋና አስደማሚ ለውጦችን የሰነደ ሲሆን ጠ/ሚኒስትሩ ያደረጓቸውን ንግግሮችና ያስተላለፏቸውን መልዕክቶችም ያካተተ መሆኑ ታውቋል፡፡ የመፅሐፉም ዋና ዓላማ፤ “ቀጣዩ ትውልድ የመደመርን ሥርዓት፣ የይቅርታንና የፍቅርን ባህል ጠንቅቆ እንዲያውቅና በተግባር ላይ እንዲያውለው፣ኢትዮጵያዊነትን እንዲለማመድ ማድረግ ነው” ይላል - በመጽሐፉ ላይ የሰፈረው ማስታወሻ፡፡ በ108 ገፆች የተቀነበበው መፅሐፉ፤ በ80 ብር ለገበያ ቀርቧል፡፡
ማንበብ ሙሉ ሰው ያደርጋል፡፡
ምንጭ፦
አዲስ አድማስ ጋዜጣ
“የማስጠንቀቂያ ደወል” ላይ ነገ ውይይት ይካሄዳል
ሚዩዚክ
ሜይዴይ ኢትዮጵያ ከኢትዮጵስ ኮሌጅ ጋር በመተባበር ነገ ከቀኑ 8፡00 ጀምሮ በአርክቴክት ሚካኤል ሽፈራው “የማስጠንቀቂያ ደወል” መፅሐፍላይ በብሔራዊ ቤተ መፃህፍትና ቤተ መዛግብት ኤጀንሲ አዳራሽ ውይይት ያካሂዳል፡፡ለውይይቱ የመነሻ ሀሳብ የሚያቀርቡት በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የገቨርናንስና ዴቨሎፕመንት ትምህርት ክፍል መምህር ሲሆኑ መድረኩን የሚመሩት አቶ ሰለሞን ተሰማ ጂ ናቸው ተብሏል።ፍላጎት ያለው በውይይቱ ላይ እንዲሳተፍ ሚዩዚክ ሜይዴይ ጋብዟል፡፡
ማንበብ ሙሉ ሰው ያደርጋል፡፡
ምንጭ፦
አዲስ አድማስ ጋዜጣ
No comments:
Post a Comment