ነበበ - ተናገረ፤ ንባብ - ንግግር ማንበብ ጮክ ብሎ ሌላው እንዲሰማው ማንበልበል ነው፡፡ መመልከት የመጽሐፉን (የጽሑፉን) መልእክት በልቡናና በአእምሮ ማሳደር
የንባብ ጥቅም
የማንበብ
ጥቅም
1. ከቀደሙት ዘመናት ጋር ያገናኛል፡፡የቀደሙት የተጻፉጽሑፎች
በዚያ ዘመን ስለነበሩ ታሪክና ሥራ በግልጽ እንድናውቅ ያደርጉናል፡፡
2. ጥሩ እውቀት እንዲኖረን ያደርጉናል፡፡
3. አንድ ወጥ ቋንቋና ዕውቀትን ያስጨብጣል፡፡የቀደሙጸሐፊዎችን አባባል እንድንጠቀምበት
ይረዳናል፡፡
4. ሰው የሦስት ዘመን ውክልና ያለው በመሆኑ ያለፉትንና የወደፊቱን እንዲኖር
ያደርጉታል፡፡
የማንበብ ጥቅሞች
በየቀኑ
ማንበብ ለምን ይጠቅማል?
1. አዕምሮን ለማንቃት
-ጥናቶች እንደሚያሳዩት ከሆነ የአዕምሮ መንቃት ከአንዳንድ በሽታዎች ለምሳሌ፡-
የአዕምሮ የመርሳት በሽታ (ALZHEMLR) እንዲሁም የአዕምሮ መሳት በሽታ (DEMENTLA) የሚያመጡትን ጉዳት በእጅጉ በመቀነስ
ረገድ እንዲሁም አስቀድሞ በመከላከል ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያደርጋል፡፡ ምክንያቱም አእምሮ ንቁና በተለያዩ ነገሮች ከተሳበ የማሰብ
ያለመርሳትና የማስተዋል አቅሙን እንዲያጣ ያደርጋል፡፡ ስለዚህ አእምሮን እንደማንኛውም የሰውነታችን ክፍል ልናንቀሳቅሰው (አካላዊ
እንቅስቃሴ) ልናደርግለት ይገባል፡፡ ይህን በማድረጋችን አእምሮአችንን ጠንካራ እና ጤናማ እናደርገዋለን፡፡ በተጨማሪም ከማንበብ
ውጪ አንዳንድ ጨዋታዎች ለምሳሌ፡-እንቆቅልሽ(ህ) ፤ ቼዝ የመሳሰሉትን የአእምሮ ንቃት የሚፈጥሩ መዝናኛዎች ናቸው፡፡
2. ጭንቀት ለመቀነስ
በቀንውሎአችን ውስጥ ከሚኖርብን ከባድ ጭንቀት በስራ ፤ይሁን በቤተሰብ፤
በግል ግንኙነት ወይም በማንኛውም አይነት ጉዳይ አንድ ጥሩ ታሪክን ማንበብ ያስጨነቀንን ስሜት ፈፅሞ እንዲጠፋ በማድረግ ከፍተኛ
ሚና ይጫወታል፡፡ እንድ በጥሩ ሁኔታ የተፃፈ (ፅሑፍ) በፅሑፉ የአንድ አንባቢ የእውቀት ዘርፍ የመቀየር ሀይል አለው፡፡ በተጨማሪም
አንድ ጥሩ የሆነ መፅሐፍ(ፅሑፍ) ካለንበት ሁኔታ ወይም በሰዓቱ እያከናወንን ባለው ድርጊት ላይ የሚረሳበት እና በፍፁም ወደ ሌላ
አለም ሄደን አየሰራን ያለውን ነገር በመርሳት የተፃፈውን ፅሑፍ እራሳችንን ከተን እራሳችንን እንደ መስታወት ያሳየን እና ጭንቀታችንን
አስወግዶ ሰውነት ከለበት የመረበሽ እና ያለመረጋጋት ስሜት እዲያፍ ያደርገዋል፡፡
3. እውቀት ለማሳደግ (ለማጎልበት)
በተለያየ
አጋጣሚ የማናነበውን ነገር ጭንቅላታችን ትናንሽመረጃዎችን እንዲያጠራቅም ያደርገዋል፡፡ እናም እነዚህ መረጃውች እየተጠራቀሙ ሲሄዱ
እውቀት ይሆናሉ፡፡ ስለዚህ ብዙ ባነበብን ቁጥር ዘርፈ ብዙ የሆነ እውቀት እንዲኖረን ያደርጋል ይህም በማንኛውም ሁኔታ በስራ ወይም
በህይወታችን ውስጥ ለሚያጋጥሙን ጥያቄውች ተገቢ አስተሳሰብ
(Logical) የሆነ ምላሽ እንድንሰጥባቸው ያደርገናል፡፡ በተጨማሪም አንድ ሰው ገንዘባችንን ፤ ንብረታችንን እንዲሁም ጤናችንን
ሊወስድብን ይችላል፡፡ ሆኖም ግን እውቀት የግል የሆነ ማንም ሊነካብን የማይችለው ሀብታችን ነው፡፡
4. የመዝገበ ቃላት ችሎታችንን ለማሳደግ (ለመጎልበት)
ይህ ከላይ
ከተጠቀሰው ጋር ይመሳሰላል፡፡ ብዙ ባነበብን ቁጥር ብዙ ቃላቶችን እናውቃለን፡፡ ይህ እለት ተእለትለሚያጋጥሙን ጉዳዮች (ሥራዎች)
መፍትሔ ለማግኘት ከፍተኛ አስተዋፅኦ አለው፡፡ጥሩ የቃላት አጠቃቀም እና የንግግር ችሎታ ያለው ሰው ለሚሰራው የሙያ ዘርፍ ትልቅ
የሆነ አስተዋፅኦ ያደርግለታል፡፡ ይህም በራሱ መተማመንን፤ ከፍ አደርጎ ሀሳቡን የመግለፅ ችሎታያጎናፅፈዋል፡፡ ብዙ የሚያነቡ ሰዎች
የተለያየ የእውቀት ዘርፍ ስለሚኖራቸው ነገሮችን ሲያጠሩ ከብዙ መንገዶች ስለሆነ ጥሩ የመፍትሔ ሰዎች የመሆን ብቃት አላቸው፡፡ ብዙ
ማንበብ ብዙ ቃላትን ብቻ ሳይሆን የተለያዩ ቋንቋዎችን ለማወቅ ቶሎ ለመማርም ይረዳል፡፡ ይህም የቋንቋውን ዘይቤያዊ አጠቃቀም በንግግር
ብቻ ሳይሆን በፅሁፍም ለመረዳት ያስችላል፡፡
5. የማስታወስ ችሎታን ይጨምራል
አንድ መፅሐፍ ስናነብ የመፅሐፉን ገፀ ባህሪዎች አመጣጥ፤ ባህርይ፤ ስኬት፤ ማንነት እንዲሁም ታሪኩ ስለተፃፈበት ሁኔታና
አካባቢ በአጠቃላይ ብዙ የሆኑ ለፅሑፍ የተጠቀሙ ነገሮችን እንረዳለን፡፡ ስለዚህ ታሪኩን ከማንበብ ጀምሮ ለመቀጠል እነዚህን የታሪኩን
ክፍሎች ማስታወስ መቻል አለብን፡፡አዕምሮ ደግሞ ግሩም የሆነ የአካላችን ክፍል ነው፡፡ እነዚህን ትንንሽ መረጃውች ሳያደባልቅ፤ ሳይተው፤
ሳያቃርን፤ ሳይሰለች የማስቀመጥ ችሎታ አለው፡፡ እነዚህን መረጃዎች በሚያስፈልገው ጊዜ እና ሰዓት ለሚያስፈልጉት ሁኔታዎች በ
(Relative thinking & Recall) ይጠቀምባቸዋል፡፡ ስለሆነም ብዙ የማንበብ ልምድ ያለው ሰው አእምሮው በደንብ
በእውቀት የጎለበተ ሰው ስለሚሆን ንቁና ፈጣን አእምሮ ያለው ሰው ይሆናል፡፡ ለፈጠራ ችሎታም ያበቃዋል፡፡
6. ጠንካራ የሆነ የማመዛዝን ችሎታ
አንድ ጥሩ የሆነ ልብ ወለድ እያነበብን በውስጡ ምስጢራዊ የሆነውን ነገር ገና መፅሐፉን አንብበን ከመጨረሳችን በፊት
ያን ምስጢራዊ ነገር እኛው እራሳችን እንፈታዋለን፡፡ ይህ ማለት አንድ ሰው በጥልቀት እና በማስተዋል አንድን ችግር የመፍታ ችሎታ
እንዲያዳብር ያደርገዋል፡፡ ይህንንም ሲያደርግ ልክ እንደሚያነበው መፅሐፍ የታሪኩን ባለቤቶች እንደሚያጠና ሁሉ ባለበት ሁኔታ ውስጥ
ያሉትንም ነገሮች በትኩረት ስለሚመለከታቸው ችግሩ የት ጋር እንደተፈጠረና ምን አይነት መፍትሔ እንደሚያስፈልገው በቀላሉ በመገንዘብለመረዳት
ያስችለዋል፡፡ ስለሆነም ጠንካራ የማመዛዘን ችሎታ በማንበብ ብቻ ሊያዳበር ይችላል ማለት ነው፡፡
7. በአንድ ሀሳብ ላይ ብቻ የሚያተኩር
ችሎታ (Concentration and focus)
የሰው ልጅ ህይወት በአሁኑ ጊዜ
በኢንተርኔት የተጠመደች ናት፡፡በአንድ ደቂቃ ውስጥ ብዙ አይነት ስራዎችን እናከናውናለን፡፡ ጥናቶች
እንደሚያሳዩት ከሆነ በ5 ደቂቃ ውስጥ አንድ ሰው ስራውን እየሰራ፤ የተላከለትን ኢሜል እየተመለከተ፤ ከሰዎች ጋር እያወራ ዘመናዊ
ስልኩን እተመለከተ ብዙ ክንውኖችን እያደረገ ይገኛል፡፡ ሆኖም ግን እንዲህ አይነት ባህርይ ወይም የስራ ክንውን በስራ ላይ የምናወጣውን
የእለት ንቃት በእጅጉ ይቀንሰዋል፡፡ ምክንያቱም ሀሳባችን ብዙ ነገሮች ላይ ስለተበታተነ አንድን ስራ በአግባቡ እና በሚገበው ሁኔታ
ማከናወን አንችልም፤ በተፈለገው ጊዜ ስራውን ልናስረክብም አንችልም፡፡
መፅሐፍ ስናነብ ግን እንደዚህ አይደለም ታሪኩ
(ፅሑፉ) በጣም ጥሩና መሳጭ ከሆነ በታሪኩ (ፅሑፉ) ከመሳባችንና ከመመሰጣችን የተነሳ ዓለም ላይ ስላለው ነገር ፈፅሞ እንረሳለን፡፡
ስለሆነም ብዙ የሚያነብ ሰው እርሱ ሳያውቀው በአንድ ነገር ላይ የማተኮር ልምድ ያዳብራል፡፡ ይህም ለሚያከናውነው ስራ ያለመሰልቸት
ቶሎቶሎ ብሎ ስራውን በተሰጠው ጊዜ በአግባቡ እንዲሰራ ያደርገዋል፡፡
8. የተሻለ የመፃፍ ችሎታ
በጥሩ ሁኔታ የተፃፈ መፅሐፍ (ፅሑፍ) የአንድ ሰው የመፃፍ ችሎታን ከማጎልበቱ በተጨማሪ ለወደፊት የመፃፍ (የፅሑፍ)
ባለቤት ለመሆን ያበቃዋል፡፡ ለፀሐፊያንም ቢሆን ለተሻለ ፅሁፍ ያበቃል፤ ያለውንም ይደግፋል፡፡
ታላላቅ ፀሐፊያን (Great Novellas) የሚባሉ በሌሎች ታዳጊ ደራሲያን ላይ እጅግ ከፍተኛ የሆነ የሙያ ተፅእኖ
አላቸው፡፡ ደራሲያን ብቻ ሣይሆን በዘርፉ ብዙ የሰሩ ገጣሚያን፤ ሙዚቀኞች፤ ሠዓሊያንም ጭምር ለታዳጊዎቹ ትልቅ የሆነ መሠረትን የሚያስቀምጡ
ሰዎች ናቸው፡፡ የእነዚህ ሰዎች ታሪክ በራሱ ከፅሁፍነት በተጨማሪ አስተማሪ፤ መካሪ፤ የሕይወት መንገድ የመሆን አቅም አለው፡፡
9. የእርጋታ (የፀጥታ) መንፈስ
አንድ ፅሑፍ (መፅሐፍ) በምናነብበት ጊዜ ውስጣችን የተለየ ሰላምናፀጥታ መንፈስ ያገኛል፡፡ እነዚህ ፅሑፎች የእምነት
መፅሐፍ፤ ልብ ወለድ፤ ኢ-ልብ ወለድ ፤ግጥም፤ የስነ ልቦና መፅሐፍት፤ ታረክ ወዘተ… ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ እነዚህ ፅሑፎች ባጠቃላይ
የአንድ ሰው ህይወት በአጋጣሚዎች ሊያስተላልፉት የሚችሉት መልዕክት አላቸው፡፤ በዚህ ሰዓት ፍፁም ሰላም፤ የእርጋታ መንፈስ፤ እንዲሁም
የደምዝውውርን ጭምር የማርገብና የማረጋጋት ሀይል አላቸው፡፤ ስለሆነም ማንበብ ጥሩ የሆነ የእርጋታ መንፈስ የሚሰጥ የሚያዝናና ልምድ
ነው፡፡
10. የማንከፍልበት መዝናኛ
መጻሕፍት የሰው ልጅ ብዙ ወጪ ሳያወጣ የሚዝናናባቸው መንገዶች ናቸው፡፡ በዚህ ዘመን ደግሞ የተለያዩመጻሕፍትን በቀላሉ
ለማግኘት የሚያስችሉ ብዙ መንገዶች አሉ፡፡የመጻሕፍትን (ፅሑፍ) አይነቶች በዚህ ጊዜ ዘርፈ ብዙ ናቸው፡፡ የፋሽን፤ የሰው ታሪክ፤
የአዋቄዎች፤ የልጆች፤ የታዳጊውች ወዘተ… በቀላሉ ማግኘት እንችላለን፡፡ ገዝተንም ብናነባቸው ከኛው ጋር ለዘለአለም የሚቀሩ ንብረቶች
ስለሆኑ ወጪአቸው እንብዛም ነው፡፡ ለአንድ ሰው ሳይሆን ለልጅ ልጅ የሚተረፉ የታሪክ አሻራዎች ናቸው፡፡
Reading
skill
Improving reading skill will reduce unnecessary
reading time and enable students to read in a more focused and selective
manner.
How
to improve reading skill
Have clear reading goals
Choose the right texts
Use the right reading style
Use note taking question
Styles/
techniques/ of reading skill
- Scanning:
◦ For a specific focus
◦ To find particular words or phrases that are relevant
to the task your are doing.
- Skimming:
◦ For getting the gist of something
◦ To get the main points and skip over the details.
- Active reading:
◦ Always make notes to keep up your concentration and
understanding
Tips for active reading
Underling and highlighting
Note Key Words
Pre-reading questions
Question based on the reading
Library
use skill
Library
Is an organized collection of resources made
accessible to a defined community for reference or borrowing.
Provide digital or physical access to materials
‹‹ንጽሕናን በሰውነት ልታሳድር ብትወድ ሁል ጊዜ በመጸለይ
መጽሐፍ በመመልከት ሐልዮ ኀጣውእን ከአልተ አርቅ፡፡››
ማር ይስሐቅ
‹‹ወደ በጎ ነገር የሚያደርሱ መጽሐፍትን ዘወትር መመልከት በጎ ነገርን ማሰብ በልቡላው ይጸናል፡፡››
ማር ይስሐቅ
‹‹ለሰውነትህ ዕረፍትን ታገኝ ዘንድ ዘወትር ቅዱሳት መጻሕፍትን
መመልከት ውደድ፡፡››
ማር ይስሐቅ
‹‹ብዙ ነገር ከመናገር ብዙ ከመመገብ የተከለከለ አፍ
የመጽሐፍትን እና የጌታን ምስጢር ይካፈላል፡፡››
አረጋዊ መንፈሳዊ
‹‹የእርሱን መጽሐፍት ባታገኙትና ጽሑፉን የምትገለብጡበት
ማንም ባይኖራችሁ በሸሚዛችሁ ላይ ጻፉት››
አንድ የስምንተኛው መቶ ክ/ዘመንአባት ስለ ቅዱስ አትናትዮስ
ሲመሰክር
No comments:
Post a Comment