ንባብ አጭር የሆነችውን ሕይወትን በረጅሙ ለመኖር
ዳዊት ደስታ ‹‹ማንበብ
ሙሉ ሰው ያደርጋል፡፡››
1. መግቢያ
መጻሕፍት የረቀቀውን አጉልትው የሚያሳዩ፣የተሰወረውን ምስጢር ገልጠው የሚያስረዱ
የእውቀትና የጥበብ ምንጮች ናቸው፡፡ይህንን ዘመን-ዘለቅ እውነታ በውል የተገነዘቡት አበው ‹‹ሁሉንም መርምሩ መልካሙን ያዙ›› በማለት
አበክረው ይመክራሉ፡፡በምክራቸውም የማያውቁትን በጥልቀት መርምሮ፣ መልካም ያሉትን አጥብቆ የመያዝን ጠቀሜታ ይጠቁማሉ፡፡
የማያውቁትን
ጠልቆ ለመመርመር፣ጠንቅቆ ለማወቅም ሆነ አጥብቆ ለመያዝ ደግሞ ከንባብ የተሻለ አማራጭ የለም፡፡ለምን ቢባል መጻሕፈትን ማንበብ ማንነትን
ከስር ከመሠረቱ ለማወቅ፣አስተሳሰብን ለመቀየር፣ሕይወትን ለመለዋወጥና ባለራዕይ ለመሆን ያስችላልና ነው፡፡በመሆኑም ማንነትን ጠንቅቆ
ለማወቅም ሆነ ዘርፈ ብዙ ጥበብን ለመገብየት የሚተጋ ማንኛውም ሰው (ዜጋ) በተለይ ደግሞ ወጣቱ ትውልድ/የመጻሕፍትን የእውቀት ማዕድ
በመቋደስ አእምሮን ማጎልመስ ይጠበቅበታል፡፡ይህ ሲሆን ብቻ ነው የሕይወት ዘመን ውጥኑን ስኬታማ ለማድረግ የሚያስችል የእውቀት አቅም
መፍጠር የሚችለው፤ብሎም በእውቀት ላይ በተመሠረተ አኩሪ ተግባሩ የትውልድና የሀገር ተረካቢነት አደራውን በአግባቡ የሚወጣው፡፡እንደመታደል
ሆኖ በያዝነው በሃያ አንደኛው ክፍለ ዘመን ለትጉህ አንባቢና ለጥበብ ፈላጊ በርካታ ምቹ ሁኔታዎች ተፈጥረዋል፡፡
2. የንባብ ባህል መዳበር ፋይዳ
ንባብ በጽሑፍ የሰፈረ ፣የዘመን-ዘለቅ እውቀትና ጥበብ የሚቀሰምበት ክህሎት
ነው፡፡ ንባብ የአእምሮ ግንባታም ነው፡፡አገር ለማልማት ቀድሞ የሰው ልጆችን ማልማት ያስፈልጋል፡፡ሰው ለማልማት ደግሞ የጽሑፍን
ማእድ ዓይነት በዓይነት ማሰናዳት ያስፈልጋል፡፡ለምን ቢሉ ጽሑፍ የማንነታችን መነሻና መድረሻ የሆነውን ታሪክ፣ቱባ ባህል፣እውቀትና
ልምድ የምንቀስምበት፣ብሎም አካባቢያዊና ዓለም አቀፋዊ ጥበብን የምንቋደስበት ድግስ ነውና ነው፡፡
ከላይ
በጥቅሱ ከቀረበው ትንተና የሰው ልጅ የንባብ ባህሉን እያዳበረ በሄደ መጠን የበርካታ አዎንታዊ ፋይዳዎች ተቋዳሽ መሆኑን ለመገንዘብ
ይቻላል፡፡
3. የንባብ ባህል ያዳበረ ግለሰብ
v -የጥበብ
ምስጢር በጥልቀት የመመርመር አእምሮአዊ ብቃቱን ያሳድጋል፡፡
v -ዘርፈ-ብዙ
እውቀትን የመገንዘብ አቅሙን ያዳብራል፡፡
v -አዳዲስ
በሚወጡ እውቀቶች የአስተሳሰብ አድማሱን ያሰፋል፡፡
v -ሕይወቱን
በግብታዊነት ሳይሆን በምክንያት ይመራል፡፡
v -በኑሮ
ውጣ ውረድ የሚያጋጥሙ ችግሮችን የመፍታት አቅሙን ያዳብራል፡፡
v -በእውቀቱ
ልክ መጥኖ የጀመረውን የሕይወት ጉዞ ለስኬት ያበቃል፡፡
v -ነገሮችን
አስፍቶ ማየት ይችላል፡፤
v -የተሰማራበትን
ሙያ የማፍቀር ጠቀሜታን ይረዳል፡፡
v -በጥድፍያ
ውስጥ ባለ ማህበረሰብ ውስጥ በአሸናፊነት የመኖርን ግንዛቤ ይፈጥራል፡፡
v -አስተሳሰቡን
በመቀየር ሕይወቱን ለመለወጥ የሚያልም ባለራእይ ይሆናል፡፡ለራእዩ እውን መሆንም የእውቀት አቅሙን ያጎለብታል፡፡እንዲሁም አጭር የሆነችውን
ሕይወቱን በረጅሙ ለመኖር ያስችለዋል፡፡
4. ሉላዊነት በመዲናችን ወጣቶች የንባብ ባህል ላይ የሚያሳድረው ተጽዕኖ
አለ ወይ?
ሉላዊነት በመዲናችን ወጣቶች የንባብ ባህል ላይ የሚያሳድረው ተጽዕኖ መኖር/አለመኖሩን
በውል ለመለየት በተጨባጭ መረጃ ላይ የተመሠረተ ጥናትና መርምር ማድረግ ግድ ይላል፡፡ይህን መሰሉ ጥናትና ምርምር መደረጉ በእጅጉ
አስፈላጊና አንገብጋቢ መሆኑም ይታመናል፡፡ይህ ሲባል ግን በመዲናችን ነዋሪ የሆኑ በርካታ ወጣቶች የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴያቸው
መሠረት በማድረግ ሉላዊነት በንባብ ባህላቸው ላይ ተጽዕኖ እያሳደረባቸው መሆን/አለመሆኑን የሚጠቁምና በአንጻራዊነት ወደ እውነታው
የሚቃረብ ግምታዊ ምላሽ መስጠት ፈጽሞ አይቻልም ማለት አይደለም፡፡በእሳቤ መነሻነት በቀጣዩ የጥናት ክፍል ሉላዊነት በመዲናችን ወጣቶች
የንባብ ባህል ላይ የሚያሳድረው ተጽዕኖ አለ ወይ? በሚል ለተነሣው ጥያቄ እንደመነሻ የሚያገለግልና በአንጻራዊነት ወደ እውነታው
እንደሚቃረብ የሚታመንበት ምላሽ የማስገኘት ጥረት ይደረጋል፡፡
የመዲናችን
እጅግ በርካታ ወጣት በየምሽቱ በዲስቲቪ አውሮፕላን አውሮፓ ደርሶ ይመለሳል፡፡ማታ ማታ የእንትናና እንትናን ኳስ ያያል፡፡ቀን በሥራ
ቦታና በትምህርት ገበታ ስለኳስ ያወራል፡፡ስለእንትና የእግር ወለምታ ሲጨነቅ ያረፍዳል፡፡በእንትና ሀትሪክ ሲፎክር ይውላል፡፡በእንትና
ድል ይደሰታልይኩራራል፡፡የድሉን ምሥራች ለልብ ወዳጁ ወይም ለቀንደኛ ተቀናቃኙ ሜሴጅ ያደርጋል፡፡በእንትን ሽንፈት ከልቡ ተበሳጭቶ
ጨጎራውን ይልጣል፡፡በሚደግፈው ቡድን ሽንፈት አምርሮ ይቆጣልበንዴት ይጦፋል፡፡ንዴቱን ቡጢ በመሰንዘርና በመፈነካከት ያበርዳል፡፡የመዲናችን
አፍላ ወጣት ተማሪ/ሠራተኛ/ ውድ ጊዜውን ኳስ በማየትና ስለኳስ በማነብነብ
ያሳልፋል፡፡ኳስ ይተነፍሳል፣ኳስ ይበላል፡፡በድል ዋንጫ እርካታ ይጨልጣል፤በሽንፈት ዋንጫ ምሬት ይጋታል፡፡በዚህም ሳቢያ በኳስ ሱስ የተጸናወተው የመዲናችን አብዛኛው ወጣት ወደ አብያተ መጻሕፍት ጎራ ብሎ
የሚያነብበት ነጻ ጊዜም ሆነ ለንባብ ፍላጎት የተነቃቃ አእምሮ ያጣል፣ሳይወድ በግዱ ከንባብ ይርቃል፡፡በመሆኑም የመዲናችን
አብዛኛው ወጣት የሉላዊነትና የኢንፎርሜሽን ኮሚንኬሽን ቴክኖሎጂ ሽግግር ውጤት የሆነው ዲስቲቪ በፈጠረለት መልካም አጋጣሚ ዓይኑን
በኳስ እያጠበ፣አእምሮውን በንበብ ረሃብ ይቀጣል፡፡የእውቀት አቅሙ ይቀጭጫል፡፡የአስተሳሰብ
አድማሱ ይጠባል፡፡ካለ አውሮፓ ኳስ ተጫዋች የዝውውር መስኮት መከፈትና መዘጋት በስተቀር በጉጉት የሚጠብቀው፣ካለ እንትና የዝውውር
ሪከርድ መሰበር በስተቀር ትኩረቱን የሚስበው ነገር ያጣል፡፡ተምሮ ለቁም ነገር የመብቃትም ሆነ በህትመት/በኤሌክትሮኒክስ/ፎርማት
የቀረቡ መጻሕፈትን አንብቦ አእምሮውን የማጎልመስ ፍላጎቱ ይሟሽሻል፡፡ከዚህ በመነሳት የዘመነ- ሉላዊነት ገጸ በረከት የሆነውን ትዕይንተ
ኳስ ለመቋደስ ቅድሚያ የሰጠው የመዲናችን አብዛኛው ወጣት መጻሕፈትን
አንብቦ የትላንት መነሻውንና የነገ መድረሻውን በውል ተገንዝቦ የመኖር ፍላጎቱና ተነሳሽነት እንዳይኖረው ጫና የሚያደርግ አሉታዊ
ፋይዳ ሰለባ ሆኖል የሚል ማጠቃለያ መድረስ ይቻላል፡፡በተለያየ ነገር ከመጠመዱ የተነሳ መጻሕፍት የሚያነብበት ነጻ ጊዜም ሆነ የማንበብ
ፍላጎት ያጣል ሳይወድ በግድ ከንባብ ይርቃል፡፡
ማጠቃለያ
በርካታ የመዲናችን ወጣቶች መጻሕፍትን በማንበብ እውቀቱና ጥበብ ከመቅሰም ይልቅ
የዘመነ-ሉላዊነት ውጤቆች ወደሆኑት ወደ ትዕይንተ የአውሮፓ ኳስና ትዕይንተ ወሲብ አድናቂነት እንደሚያዘነብል ለመገንዘብ እንደተቻለ
በጽሑፉ ለማሳየት ተሞክሮል፡፡በዚህም የማንነቱ መገለጫ ለሆነው ታሪክና ቱባ ባህል ባይተዋርነት እንደተዳረገና በምክንያት ሳይሆን
በግብታዊነት ለመኖር እንደተገደደ ግንዛቤ ተወስዶአል፡፡ይህ ትውልድ የንባብ ፍቅር አድሮበት አእምሮውን እውቀትና ጥበብ እየመገበ
የመኖር ፍላጎትና ተነሳሽነት እንዲያድርበት ወላጆች፣በየደረጃው ያሉ የትምህርት ተቋማትና ብሔራዊ ቤተ መዛግብትና ቤተመጻሕፍት ኤጀንሲ
የተጣለባቸውን ቤተሰባዊና ተቋማዊ አደራ በአግባቡ መወጣት ይጠበቅባቸዋል፡፡
ይህንን
በማድረጋቸውም ከመጻሕፈት ንባብ የሚቀስመው እውቀትና ጥበብ ማንነቱን ጠንቅቆ የሚገነዘብ፣የቀደመው ትውልድ ተንከባክቦና ጠብቆ ያቆየውን ሀገራዊ
ቅርስ የሚያከብርና ታታሪነቱንና አርአያነቱን በተግባር የሚያስመሰክር ባለራእይ ወጣት ትውልድ ይፈጥራሉ፡፡የመዲናችን ወጣት ትውልድ
ከሚያፈዘው ትእይንተ የአውሮፓ ኳስና ውዥንብር ላይ በመጣል ዕድሜውን በአጭሩ ለሚቀጭ አደጋ ከሚያጋልጠው
ትዕይንተ ወሲብ ፊልም ይታደጋሉ፡፡ ከመጻሕፍት የሚቀሰም እውቀትና ጥበብ ትውልዱን ገደብ ሊያበጅለት ከሚገባው አጎጉል ዝንባሌው ለመጠበቅ
የሚያስችል ጥቅምና አቅም እንዳለው ያደርጋሉ፡፡ከንባብ እውቀትና ጥበብ እንዲቀስምና መልካም ፍሬ እንዲያፈራ በመምከር የመዲናችንን/የሀገራችንን/ወጣት
ትውልድ ከጥራዝ ነጠቅ ፈረንጅ አድናቂነት አደጋ ለመታደግ እንረባረብ፡፡
ምንጭ-ያሲን
ዑመር ፣ባህል ‹‹ሉላዊነት፣ወጣትነትና ንባብ››፣ፈለገ ጥበብ፡፡2002(ተቀንጭቦ የቀረበ)
1. ንባብና የንባብ ልምድ
ዳዊት ደስታ
‹‹ማንበብ ሙሉ ሰው ያደርጋል፡፡››
1.1
ንባብ ምንድን ነው?
ንባብ
በራሱ ውስብስብ ሂደት ነው፡፡ ረቂቅ የሆነ አዕምሮአዊ ሂደት በውስጡ የማጠቃለሉ ሁኔታ ነው ሂደቱን ውስብስብ ያደረገው፡፡ እንደ
ሐመር /1991 ዓ.ም/ አገላለጽ ንባብ እንደ ማዳመጥ ሁሉ ከውጭው ዓለም ወደ ውስጣችን የተለያየ ልምድ፣ እውቀትና ብልሃት የምንገበይበትና
የመናሰርጽበት ውስብስብነት የሚታይበት መረጃ የመቀበያ ክሂል ነው፡፡
1.2
ሰዎች ለምን ያነባሉ?
ጠቅለል
ባለ መንገድ ንባብ የተለያየ ልምድ፤ ዕውቀትና ብልሃት የምንገበይበትና የምናሰርጽበት የመቀበያ ክሂል ነው ብንልም የራሱ የሆነ ግቦችና
ዓላማዎች ያሉት መሆኑ መዘንጋት የለበትም፡፡ ግሬሊት /1981/ ሰዎች ለምን ያነባሉ? የሚለውን ጥያቄ በማንሳት የንባብን መሠረታዊ ዓላማዎች እንደሚከተለው ትዘረዝራለች፡፡
1.2.1 ሰዎች ለጥንቃቄ ወይም
ራስን ከአደጋ ለመከላከል በሚል ያነባሉ
ለመጠንቀቅ
ወይም ራሳችንን ከአደጋ ለመከላከል ስንል የምናነብበት አጋጣሚ አለ፡፡ ለምሳሌ ከዚህ የሚከተሉትን መሰል ነገሮች ያለማንበብ ለችግር
ወይም ለአደጋ ያጋልጣል፡፡
Ø ቁም
Ø ፎቶግራፍ ማንሳት ክልክል ነው
Ø መግባት ክልክል ነው
Ø ከክፍሉ ሠራተኞች በስተቀር … ወዘተ
እነዚህንና እነዚህን መሰል ጽሑፎች በተለያዩ ቦታዎች እንመለከታልን፡፡ የተጻፉበትንም
ትልቁ ምክንያት ሰዎች የተጠቀሰውን ነጥብ ተላልፈው ለችግርና ለአደጋ እንዳይጋለጡ ለመርዳት ነው፡፡ አንባቢም ጽሑፎቹን ተመልክቶ
አስፈላጊውን ጥንቃቄ ያደርጋል፡፡
ሰዎች
ራሳቸውን ለማስደሰትና ለማዝናናት ያነባሉ፡፡ እንደ ልብወለድ፣ ረጅም ልብወለድ አጭርልብ ወለድ/፣ ተውኔት፣ ግጥም ወዘተ… የመሳሰሉ
ኪናዊ ሥራዎች የሚነቡበት ራስን ለማስደሰትና ለማዝናናት ሲታሰብ ነው፡፡ በኪናዊ ሥራዎች ውስጥ፣ ደራሲው የቀረጻቸው ገጸ-ባህርያት በተሳሉበት ምናባዊ ዓለም ውስጥ የሚያደርጉት
ልብ አንጠልጣይ እንቅስቃሴ ለአንባቢው አዕምሮ ምናባዊ ፍስሐ ያጎናጽፋሉ፡፡ በአጠቃላይ አንባቢው አንዲገረምና በገፀ-ባህርያቱ ውስጥ
ራሱን እንዲመለከት ያደርጋል፡፡ ነገር ግን በዚህ ሂደት ውስጥ ከደስታ በስተቀር የሚገኝ ሌላ ነገር የለም ብለን ማጠቃለል የለብንም፡፡
በዚህ
ዓይነቱ የንባብ ሂደት ውስጥ ከሚገኘው የደስታ ስሜት ጎን ለጎን አዳዲስ ቃላትን፣ ለየት የለ የአጻጻፍ ስልትን፣ የሐሳብ አወራረድንና
አደረጃጀትን መማር ይቻላል፡፡ እንዲህ ዓይነቱም ልምድ በቋንቋ የመጠቀም ብቃታችንን ከማሳደጉም በተጨማሪ ለፈጣን የአነባበብ ስልት
መዳበር፣ ለሂሳዊ አስተሳሰብና ሚዛናዊ አስተሳሰብ መጎልበት የሚኖረው ድጋፍ ከፍ ያለ ነው፡፡
1.2.3 አዲስ ነገር ለመማር፣
ለማወቅና ለማገናዘብ ስንል እናነባለን
ሰዎች የሚያነቡት ራሳቸውን ከአደጋ ለመከላከልና ለመደሰት ሲሉ ብቻ አይደለም፡፡
እንዲያውም ብዙ ጊዜ የሚያነቡት ለዚህ ሲሉም አይደለም፡፡ ሰዎች ብዙ ጊዜ የሚያነቡት አዲስ ነገር ለመማር፣አመጣጡን ለመረዳት፣ አካባቢውን
በበለጠ ለመገንዘብና አጠቃላይ እውቀትን ለማስፋት ሲባል ሰዎች አዘውትረው ሲያነቡ ይታያሉ፡፡ ለዚህም ነው አዲስ ነገር ለመማር፣
ለማወቅና ለማገናዘብ ስንል የምናጠፋው ጊዜ ብዙ ነው የሚባለው፡፡ ይህ የንባብ ሂደት ለንባብ ከምናውለው ጊዜ አብዛኛውን የሚሸፍን
ነው በሚል በቅድሚያ የተገለጸውም ለዚህ ነው፡፡ ከፍ ሲል የተጠቀሱት ነጥቦች ለምን እናነባለን ለሚለው ጥያቄ መልሶች ሊሆኑ ይችላሉ፡፡
ነገር ግን እነዚህ የንባብ አነሳሽ ምክንያቶች የተነጣጠሉ ተደርገው ሊታዩ አይገባም፣ ተደጋጋፊ ናቸው፡፡ ለመደሰት ስንል የምናነበው
ንባብ አዲስ እውቀት ሊያስገኝልን ይችላል፣ ለእውቀት ስንል የምናነበው ጽሑፍ እንድንደሰት ሊያደርገን ይችላል፡፡ ይሁን እንጂ ከፍ
ሲል በተጠቀሰው መንገድ የንባብ ተጠቃሚ ለመሆን ሥር የሰደደ የንባብ ልምድ አስፈላጊ ነው፡፡ ለመሆኑ የንባብ ልምድ ምንድን ነው
እንዴትስ ይዳብራል ከዚህ በመቀጠል አጠር አድርጎ ለመዳሰስ ይሞከራል፡፡ የንባብ ልምድ ጠቃሚ ተብለው ከሚፈረጁት ልምዶች አንዱ ነው፡፡
የንባብ ትምህርት ዓላማም ይህንን ልምድ በማዳበርና በማበልጸግ ላይ ያተኩራል፡፡ ትምህርት ቤቶቻችን ይህንን ልምድ በማዳበር ረገድ
ምን ያህል የበኩላቸውን ተወጥተዋል
1.3
የንባብ ልምድ
ስለ ንባብ
ልምድ ከማውራታችን በፊት በቅድሚያ ልምድ ምንድን ነው የሚለውን ጥያቄ መመለስ ተገቢ ይሆናል፡፡ የመስኩ ምሁራን እንደሚገልጹት ልምድ
ወደዚህ ዓለም ስንመጣ ይዘን የመጣነው ተፈጥሮን የምንመረምርበትየምናሻሽልበት፣ የምናሳድግበትና የምናዳብርበት አብሮን የነበረ፣ አሁንም
ያለ ወደፊትም አብሮን የሚኖር ከተግባርና ከተሳትፎ የሚመነጭ ክስተት ነው፡፡ አንድ ሕፃን ወደዚህ ዓለም ሲመጣ ምንም ያልተቀረፀበት
ግን ለመልመድና ለመማር ዝግጁ የሆነ ልሙጥ አዕምሮ ይዞ ነው፡፡ በዚህ ልሙጥና ዝግጁ አዕምሮ ላይ በመመዝገብ ሰብአዊ እድገቱን የሚያፋጥንበት
መንገድ ሂደት ደግሞ ልምድ ምስረታ ይባላል፡፡ ልምድ ምስረታ ባይኖር ኖሮ ምኑንም እንደማያውቅ አራስ ልጅ ሆነን እንቀርነበር፡፡
ያለ ልምድ ምስረታ የምናከናውነው ነገር በሙሉ ግብታዊ ሆኖ በቀረ ነበር፡፡ ወይም ደግሞ ሁልጊዜ------- እንዴት መፈጸም እንደሚገባን
በማሰብ ጊዜያችንን የምናጠፋ ብኩኖች ሆነን እንቀር ነበር፡፡ ወይም ደግሞ እንደ እንስሳት ደመነፍሳዊ ተንቀሳቃሾች እንሆን ነበር፡፡
ለዚህ ነው የሰው ልጅ ህይወት ያለ ልምድ ምስረታ ሊታሰብ አይችልም የሚባለው፡፡
ልምድ
በተለያየ መንገድ ሊመሠረት ይችላል፡፡ ዋነኛው የልምድ መመስረቻ መንገድ ደግሞ ነገሮችን በተደጋጋመሚ ማከናወን ነው፡፡ ነገሮች በተደጋገሙ
ቁጥር በአዕምሮ ውስጥ ሰርፀው የመግባት እድል ያገኛሉ፡፡ በአዕምሮ ውስጥ ሰርፆ የገባ ነገር ደግሞ በቀላሉ የማይላቀቁት
ይሆናል፡፡ ይህን መሠረት በማድረግም ምሁራን ልምድ ፍፁም ልምድና ውስን ልምድ ብለው በሁለት ይከፍሉታል፡፡ ፍፁም የሆነ ልምድ ስር የሰደደ ልምድ ነው፡፡ ውስን ልምድ ግማሹን በቀነስን ቁጥር ወይም ከድርጊቱ በራቅን ቁጥር ሊከስም የሚችል የልምድ ዓይነት ነው፡፡
ይሆናል፡፡ ይህን መሠረት በማድረግም ምሁራን ልምድ ፍፁም ልምድና ውስን ልምድ ብለው በሁለት ይከፍሉታል፡፡ ፍፁም የሆነ ልምድ ስር የሰደደ ልምድ ነው፡፡ ውስን ልምድ ግማሹን በቀነስን ቁጥር ወይም ከድርጊቱ በራቅን ቁጥር ሊከስም የሚችል የልምድ ዓይነት ነው፡፡
እያንዳንዳችን
ልብ አንለውም እንጂ የበርካታ ልምዶች ባለቤት ነን፡፡ አንዳንድ ልምዶችን በሙሉ ንቃት የምናከናውናቸው ሲሆን አንዳንዶቹ ደግሞ ሳናስተውል
የምንፈጽማቸው ነው፡፡ ለምሳሌ ያህል የንባብ ልምድ፣ የጽህፈት ልምድ፣ የንግግር ልምድ ወዘተ… የመሳሰሉት በማስተዋል የሚከናወኑ
ሙሉ ንቃት የሚጠይቁ ልምዶች ናቸው፡፡ በአንፃሩ ደግሞ እጅን ኪስ የመክተት ልምድ፡ አፍንጫን የመጎርጎር ልምድ፣ ፊትን የማበስ ልምድ፣
የአመጋገብ ባህርይ ወዘተ… ሳናስተውል የምናከናውናቸው ልምዶች ናቸው፡፡
እንደ
ማህበረሰቡ ዕይታ ጠቃሚ ወይም ጎጂ ተብሎ በሁለት ሊከፈል ይችላል፡፡ ጠቃሚ የሚባለው ልምድ በበጎ ጎኑ ድግግሞሹን በማጠንከር ማጎልበት
ሲቻል፤ ጎጂ የሚባለው ልምድ ደግሞ በተቃራኒው የምጥፎ ጎኑን ድግግሞሽ በመቀነስ ወይምጨርሶ በማጥፋት ማስወገድ ይቻላል፡፡ ለምሳሌ
ሲጋር የማጨስ ድግግሞሽ በጨመረ ቁጥር ልምዱም ያን ያህል ሥር እየሰደደ ነው የሚመጣው፡፡ የሚጨሰው ሲጋራ መጠን ሲቀንስ ወይም ጨርሶ
ሲቆም ደግሞ ቀላል ባይሆንም ልምዱ ሊሰበር ይችላል፡፡የንባብ ልምድ ጠቃሚ ተብለው ከማፈረጁት ልምዶች አንዱ ነው፡፡ የንባብ ትምህርት
ዓላማም ይህን ልምድ በማዳበርና በማበልፀግ ላይ ያተኩራል /ስሚዝና ኤሌይ 1997/፡፡ ይህ ዓይነቱ ልምድ ይዳብርና ይበለፅግ ዘንድ
ደግሞ ሰዎች ወደ ንባብ መቅረብ ይገባቸዋል፡፡ ሰዎች ወደ ንባብ እየቀረቡ ሲመጡ ለንባብ የሚቀመጡበት ጊዜ እየሰፉ ይመጣሉ፡፡ የሚያነቡትም
ነገር በመጠንና በገጽ ይጨምራል፡፡ እንግዲህ ሰዎች ለንባብ የሚመድቡት ጊዜ ሲሰፋና የሚነበቡትም መጽሐፍት፣ መጽሔት፣ ጋዜጣ፣ ወዘተ…
በዓይነት በቁጥር እየጨመረ ሲመጣ ነው የንባብ ልምድ አዳብረዋል ተብሎ ሊጠቀስ የሚችለው፡፡
ስሚዝና
እሌይ /1997 ዓ.ም/ የተሰኙ ምሁራን የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎችን የንባብ ልምድ ካጠኑ ከመረመሩ በኋላ በጥናቱ ውስጥ የታቀፉት
ተማሪዎች 19.3% ያህል በሳል አንባቢዎች፣ 59% መካከለኛ አንባቢዎች፣ 22% ያህሉ ደግሞ ዳተኛ አንባቢዎች ሆነው አንዳገኟቸው
አመልክተዋል፡፡አጥኚዎቹ በትምህርት ቤት ከማታዘዙት መጻሕፍት ባሻገር በንባብ ለመዝናናትና ለመደሰት አቅደው የሚያነቡ እነማን ናቸው?
የሚለውን ጥያቄመሠረት በማድረግ አንባቢዎችን እንደሚከተለው ለመከፋፈል ሞክረዋል፡፡ በወር ሦስትና አራት ወይም ከዛ በላይ መጻሕፍትን
የሚያነቡትን ሰዎች በሳል አንባቢ በሚል ምድብ ውስጥ ሲያስቀምጧቸው፣ በወር አንድ ወይም ሁለት መጻሕፍት የሚያነቡትን ደግሞ መካከለኛ
አንባቢ፣ በወር ምንም መጻሕፍት የማያነቡትን በንባብ የማይደሰቱትን ደግሞ ዳተኛ አንባቢ በሚል ምድብ ውስጥ አስቀምጠዋቸዋል፡፡ በጥናቱ
መሠረት ዳተኛ አንባቢዎች በትምህርት ቤት የሚታዘዙትን የመማሪያ መጽሐፍት ጭምር እየተናነቃቸው የሚያነቡ አሊያም ለማንበብ የሚያንገራግሩ
ጭምር ናቸው፡፡ ይህ ደግሞ የንባብ ልምድን ካለማዳበር የሚከሰት ነው፡፡
1.4
ጥሩ ሥር የሰደደ የንባብ ልምድ መገለጫዎች
ሥር የሰደደ
የንባብ ልምድ መታየት የሚጀምረው አንድ ሰው መስህብነት ያለው መጽሐፍ መርጦ ያለ ምንም አስገዳጅ ሁኔታ በራሱ ውስጣዊ ግፊት ተነሳስቶ
ማንበብ ሲጀምር ነው፡፡ በዚህ ዓይነት መንገድ ማንበብ የጀመረ አንባቢ የተዋጣለት አንባቢ፣ ንባቡም የተዋጣ እንደሚሆን አያጠራጥርም፡፡
እንዲህ ዓየነቱ የተዋጣ ንባብ ደግሞ ከዚህ በሚከተሉት ሁኔታዎች ይገለጻል፡፡
1.4.1 ከፍተኛ የንባብ ፍላጎት
ጥሩ የማንበብ
ልምድ ያዳበረ ሰው በእጆቹ የሚገቡት ለደረጃውና ለእድሜው የሚመጥኑት መጻሕፍት፣ ጋዜጦች ወዘተ… የማንበብ ጉጉት ያድርበታል፡፡ በመሆኑም
እነዚህና የመሳሰሉት የሚነበቡ ነገሮች ገዝቶም ሆነ ተውሶ ሲያነብ ማየት የተለመደ ነው፡፡ ከንባብም በኋላ ያነበብነውን ቁም ነገር
ለጓደኞቻችን ለማጋራት ፍላጎት ይኖረናል ይኖረዋል፡፡
1.4.2 የንባብ ፍጥነት
ጥሩ የማንበብ
ልምድ ያዳበረ የሚባለው ሰው በፍጥነት ማንበብ ይችላል፡፡ በጥናት እንደተደረሰበት ፈጣን አንባቢ የሚባለው 600 ቃላትን በደቂቃ
ያነባል፡፡ ይህም በደቂቃ 200 ቃላት ወይም በታች ከሚያነቡት ዳተኛ አንባቢዎች እጅግ የላቀ ነው፡፡
1.4.3 የንባብ ስልትን መቀያየር
ስለመቻል
ጥሩ የማንበብ
ልምድ ያዳበረ ሰው በሚያነብበት ጊዜ እንደ ንባቡ ዓላማና እንደሚያነበው ቁም ነገር የአነባበብ ስልቱን መቀያየር የሚችል ነው፡፡
በመሆኑም በቀላሉ ከግርፍ ወደ አሰሳ ንባብ፣ ከሰፊ ወደ ጥልቅ ንባብ ወይም በተቃራኒው እንደ አስፈላጊነቱ እየለዋወጠ እያለ ማንበብ
ይችላል፡፡ በዚህ ዓይነት መንገድ የሚያነብ ሰው የማንበብ ችሎታው የላቀ ነው፡፡
1.4.4 ድምፅን ከፍ አድርጎ
በእርጋታ ማንበብ መቻል
ጥሩ የማንበብ
ልምድ ያዳበረ ሰው በለሆሳስ ከሚያደርገው ንባብ በተጨማሪም በጮክታ ንባብ ጥሩ አቀራረብ ያሳያል፡፡ እንዲህ ዓይነቱ አንባቢ ድምፁን
መጥኖና ወደ አድማጮቹም አልፎ አልፎ እየተመለከተ በርጋታ ማንበብ ይችላል፡፡
1.4.5 ዘና ያለ ንባብ
የማንበብ
ልምድ ያዳበረ አንባቢ በሚያነብበት ጊዜ ፊቱ ላይ የመጨነቅ ስሜት አይታይበትም፣፣ እንዲህ ዓይነቱ አንባቢ በለሆሳስ ንባብ ወቅትም
ሆነ በጮክታ የንባብ ወቅት ስሜቱ ዘና ብሎ ይታያል፡፡ ከፍ ሲል የተዘረሩት ነጥቦች ጥሩ የማንበብ ልምድ ያዳበረ ሰው ወይም የተዋጣለት
አንባቢ የሚያሳያቸውን ባህርያት ያመላክታል፡፡ ታዲያ እንዲህ ዓይነቱን አንባቢ ለመፍጠር ምን መደረግ ይኖርበታል?
1.5
የንባብ ልምድን ለመገንባት የሚያግዙ ነጥቦች
ጥሩ የማንበብ
ልምድ ያለው አንባቢ መፍጠር ይቻል ዘንድ ጥረት መደረግ ያለበት ከዝቅተኛ ክፍሎች ጀምሮ ነው፡፡ በመሆኑም ከዚህ በሚከተሉት ነጥቦች
ላይ ትኩረት ማድረግ አስፈላጊ ነው፡፡
1.5.1 በመፅሐፍ በመጻሕፍት
ምርጫ ላይ እገዛና ጥቆማ ማድረግ፤
ተማሪዎች
የማንበብ ፍላጎት እንዲኖራቸው ብሎም የማንበብ ልምድ ማዳበር እንዲችሉ ከአቅማቸው፣ ከደረጃቸውና ከፍላጎታቸው ጋር አብሮ የሚሄደውን
ለይተን ልንጠቁማቸው ይገባል፡፡ በዚህ መሠረት ተማሪዎቻችን በሚያደርጉት የመጻሕፍት ምርጫ ላይ ከዚህ የሚከተሉትን ነጥቦች መሠረት
አድርገን ልንረዳቸው ይገባል፡፡
Ø የትኛው
መጽሐፍ ከተማሪው እድሜ ጋር አብሮ ሊሄድ ይችላል?
Ø የትኛው
መጽሐፍ ከተማሪው ደረጃና ችሎታ ጋር የተመጣጠነ ነው?
Ø የትኛው
መጽሐፍ ከተማሪው ባህልና አካባቢ ጋር አብሮ ሊሄድ ይችላል?
Ø ከተማሪው
የቋንቋ ችሎታ የማይልቅ የቋንቋ አጠቃቀም ያዘለው የትኛው መጽሐፍ ነው?
Ø የትኛው
መጽሐፍ ተማሪው በመደበኛ ትምህርት ቤት የተማረውን ትምህርት ሊደግፍ ወይም ሊያጠናክር ይችላል?
Ø ተማሪው
በጉጉት ሊያነበው የሚችለውንና ከፍላጎቱ ጋር አብሮ የሚሐደው መጽሐፍ የትኛው ነው?
Ø በቅርቡ
ታትሞ የወጣውና ያልተሰለቸ ይዘት ያለው የትኛው መጽሐፍ ነው?
መምህሩ
እነዚህን የመሳሰሉትን ጥያቄዎች በአእምሮው በመያዝ ተማሪውን በመፅሐፍ ምርጫ ሊያግዘው ይገባል፡፡ እንዲህ ዓይነት ድጋፍ የማይደረግለት
ተማሪ ከእድሜው፣ ከደረጃውና ከችሎታው ጋር የማይመጣጠነውን መፅሐፍ በመምረጥ ተስፋ የመቁረጥና ለንባብ ጥላቻ የማሳደር ስሜት ሊፈጠርበት
ይችላል፡፡ ለዚህ ደግሞ የመምህሩ ድጋፍ ሁልጊዜ ሊለየው አይገባም፡፡ መምህሩ ተፈላጊውን ድጋፍ ማድረግ እንዲችል ከተማሪው የላቀ
የማንበብ ልምድ ያካበተ ሊሆን ይገባል፡፡ የማንበብ ልምድ የሌለው መምህር ከፍ ሲል የተጠቀሱት ነጥቦች መሠረት አድርጎ ተማሪዎቹን
በሚፈልገው መንገድ ማገዝ አይችልም፡፡
1.5.2 የቡድን ንባብን ማደፋፈር
ሌላው
የንባብ ፍላጎት ማሳደሪያ መንገድ የቡድን ንባብን ማጠናከር ነው፡፡ መምህራን ክፍል ውስጥም ሆነ ከክፍል ውጭ ተማሪዎች በቡድን የሚያነቡበትን
መንገድ በቀላሉ ማመቻቸት ይችላል፡፡ በእንዲህ ዓይነቱ የቡድን ንባብ ተማሪዎች አንድን ፅሑፍ በጋራ አንብበው በመወያየት ያነበቡትን
በሚገባ እንዲረዱና የንባብ ዘዴ ወይም ብልሃት እንዲለዋወጡም ማድረግ ይቻላል፡፡ የቡድን ንባብ ከፍ ሲለ ከተጠቀሰው አገልግሎቱም
በተጨማሪ ብዙ ተማሪዎች በቡድን ከፋፍለው እያንዳንዱን ቡድን በቀላሉ ለመከታተል ያስችላል፡፡
1.5.3 ንባብ ውድድሮችን ለማካሔድ
ቀደም
ሲል በተራ ቁጥር 1.5.2 ሥር የተጠቀሱትን ነጥቦች መነሻ በማድረግ ለተማሪዎቹ ይበጃል የተባለውን መፅሐፍ መርጠን ከጠቆመ በኋላ
ተግባራችን እነዚህ ላየ ማቆም የለበትም፡፡ ተማሪዎቹ ተመርጠው የቀረበላቸውን መፅሐፍ በትክክል ማንበብ አለማንበባቸውን የአንብቦ
መረዳበት ጥያቄዎችን ቀርፆ በመጠየቅ መከታተል ይቻላል፡፡ በዚህ መሠረት ከተጠቆሙት መጻሕፍት ውስጥ አንብቦ መረዳት ጥየቄዎችን በማውጣትና
ተማሪዎቹን በመጠየቅ ብዙ ጥያቄዎች መለሱትን እየሸለሙ ማበረታታት ተገቢ ነው፡፡በዚህ ረገድ በተለይ በመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶች
የሚማሩ ተማሪዎች ከእድሜያቸውና ከሥነ ልቦናዊ ባህርያቸው በመነጨ የመፎካከርና የእኔ አበልጥ የእኔ እበልጥ ስሜታቸው ላቅ ብሎ የሚታይበት
በመሆኑ ይህንን አጋጣሚ መጠቀም ይቻላል፡፡ ይህንን የተፎካካሪነት ሥነ ልቦናዊ ባህርያቸውን መሠረት ባደረገ መንገድ የንባብ ውድድሮችነ
ማካሄድና በልጠው የተገኙትን በመሸለምና በማበረታታት ትልቅ ውጤት ማግኘት ይቻላል፡፡
1.5.4 የንባብ ዘገባ አንዲቀርብ
መጠየቅ
የንባብ
ዘገባን መምህራን የተማሪዎቻቸውን የንባብ ባህል ለማሳደግና የንባባቸውን የጥራት ደረጃ ለመለካት በሰፊው ሲጠቀሙት ይታያል፡፡ አልፎ
አልፎም ወላጆች ወይም አሳዳጊዎች የንባብ ዘገባን እንደ ---- እንደ መከታተያ መንገድ አድርገው ይገለገሉበታል፡፡ የንባብ ዘገባ፣
ንባብን መሠረት በማድረግ ትንተናና ግምገማን ስለሚያጠቃልል በየፈርጁ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ያተኩራል፡፡ ስለዚህ የተደረገውን ንባብ
መሠረት በማድረግ የምርመራና የምዘና፣ የማነፃፀርና የመወሰን ችሎታንም ለማጎልበት ይረዳል ማለት ይቻላል፡፡
1.6
የንባብ ልምድ እንዳይዳብር የሚያደርጉ መሠረታዊ ችግሮች
በንባብ
ጊዜ የሚያጋጥሙ በርካታ ችግሮች አሉ፡፡ የእነዚህን ችግሮች መነሻ ምክንያት ለይተን ካላወቅን ችግሮቹን ልንፈታ አንችልም፡፡ ከዚህ
በማስከተል ዋና ዋና የሚሰኙትን በንባብ ጊዜ የሚያጋጥሙ ችግሮች ለመጠቆም ይሞከራል፡፡
v የሰለጠነ መምህር አለመኖር
v በሥርዓተ ትምህርት ቀረፃ ላይ የሚታዩ ግድፈቶች
v የህፃናት የሥራ ጫና ከፍ ማለት
v የመጻሕፍት አቅርቦት አንሳ መሆን
v የቴሌቭዥን፣ የቪዲዮና የኮፒውተር ጨዋታዎች መስፋፋት፣
v የመጻሕፍት የሥርጭት አውታሮች ቁጥር አናሳ መሆን
v የቤተ መጻሕፍት አለመስፋፋት
v በህብረተሰቡ ዘንድ ለንባብ ያለው አመለካከት የተዛባ መሆን
v መገናኛ ብዙሃን ለመፃሐፍትና ለንባብ ትኩረት መንፈግ
v የሰዎች ንባብ ፍላጎት ማጣት
የማንበብ ፍላጎት ለንባብ ችሎታ መዳበር አንዱና ትልቁ መሠረት ነው፡፡ ሰዎች ፍላጎቱ
ከሌላቸው አንብቡ ስለተባሉ ብቻ አያነቡም፡፡ ካለፍላጎቱ እንዲያነብ የሚገደድ ተማሪም ምናልባት ገፆቹን በእጁ ሲገልጥ ይታያል እንጂ
በእርግጥ እያነበበ ስለመሆኑ የሚያሳየው ምልክት ላይኖር ይችላል፡፡ ለዚህ ዓይነቱ ችግር የውድድር ስሜት በመፍጠርና በማበረታታት፣
አስደናቂና አጓጊ ታሪኮችን ያዘሉ ፅሑፎችን በማቅረብ፣ የአንብቦ መረዳት ጥያቄዎች በማቅረብ በአግባቡ መመለሳቸውን በመከታተል ተማሪዎችን
ሊያነቃቃ ይችላል፡፡ ከዚህ በቀር ተማሪዎች እንዲያነቡ የማድረጉ ጉዳይ ፍላጎት የሌላቸውን ተማሪዎች ለማነቃቃት እንደሚያስችል መዘንጋት
አይኖርብንም፡፡
ዳዊት ደስታ ‹‹ማንበብ ሙሉ ሰው ያደርጋል፡፡››
የማንበብ ፍላጎታችን ለምን ቀነሰ?
(በከበደ ኃይሌ)
ማንበብ ሙሉ ሰው ያደርጋል፡፡
የቀድሞ ቅኝ ገዢዎችና አሰሪ ከበርቴዎች እነሱ ብቻ የተማሩ ሰዎች ሆነው እንዲታዩና እንዲከበሩ፤ ሠራተኞቻቸው የመብት ማስከበር ጥያቄ እንዳያነሱ፤ የአሰሪዎችን ሙያ እንዳይቀስሙ የማንበብና የመጻፍ ችሎታ ያላቸውን ግለሰቦች በሠራተኛነት አይቀጥሩም ነበር፡፡ የተቀጠሩትም ሠራተኞች መጽሐፍ በእጃቸው ላይ ከተገኘ ወይም ሲያነቡ ከታዩ ችግር ውስጥ ትገባላችሁ እየተባለ ይነገራቸው ስለነበር ተምሮ እንዳልተማረ ሰው ሆነው መታየት የህዝቡ የወቅቱ መታወቂያቸው እንደነበር በሥርዓቱ ውስጥ ያለፉ አገሮች በታሪክ
መዝግበውታል፡፡
የአሁኑ ጊዜ በጸረ-ንባብ የተከበበው ህብረተሰብ ከላይ ጊዜው ያለፈበት ሥርዓት የሚደርስበትና ማንበብ ነውር ነው የተባለ ይመስል የማንበቢያ ጊዜ የለኝም እያለ የነበረውን የማንበብ ባህል ልምዱ ያለቅጥ እያወረደው መታየቱ ለተመልካቹም ሆነ ለሰሚው ግራ የሚያጋባ ጉዳይ ሆኗል፡፡ ይሁን እንጂ ይህንን አቋም ይዞ የሚከተለው ህብረተሰብ ያለውን ትርፍ ጊዜ የሚያሳልፈውና የሚዝናናው ቴሌቪዠን በመመልከት፤ በኢንትርኔት የሚተላለፉት ቁንጽል ጽሁፎችን በማንበብ መጽሐፍና ወቅታዊ ጽሑፋ-ጽሁፎችን ማንበብ ጊዜው ያለፈበት ነገር አድርጎ ቆጥሮታል፡፡
በኢኮኖሚ ያደገውን አገር ህብረተሰብ ስንመለከት መጽሐፍ የሚያነብ ፍቅር ያደረበት ዜጋ ስለሆነ ያለውን ትርፍ ጊዜ ላለማጥፋት ሲል በሕዝብ ማመላለሻ ውስጥ እንኳን እያነበበ ሲጓዝ ይታያል፡፡ መጽሐፍ፤ጋዜጣና መጽሄት ከእጁ የማይለየውና በማንበብ እውቀት የሚገበይበት አንዱ መንገድና ሁነኛ መሣሪያ ሆኖ ስላገኘውና ጥቅሙን ጠንቅቆ ሰለተረዳ የማንበብ ልምዱን ሥራዬ ብሎ ተያይዞታል፡፡ ምክንቱም የሰው ልጅ ትምህርት የሚገበየው ትምህርት ቤት በመሄድ ብቻ ያለመሆኑን ላልተማረው ህብረተሰብ ለማሳወቅና ለማነቃቃት፤ትምህርትን ለማስፋፋትና በአንጻሩም መሃይምነትን ለማጥፋት፤ ለደራሲዎች ሞራል ለመስጠት፤ የጻሐፊዎችን ቁጥር ለመጨምር፤ የአታሚ ደርጅቶችን ህልውና ለማራዘም፤ ለታዳጊው ወጣት ምሳሌ ሆኖ ለመታየት ጭምር ነው፡፡
ከዚህም በተጨማሪ ደራሲዎችና አታሚዎች ለህዝብ ግልጋሎት ያሳተሙትን ጽሑፎች ለአንባቢያን ለማሳወቅ ጥረት ሲያደርጉ ህብረተሰቡ ደግሞ በሥፍራው ላይ ተገኝቶ ባይገዛም እንኳን በማጀብ የደራሲዎችን፤ የጽሁፍ አታሚዎችንና የፕሮግራም አዘጋጆችን
ሞራል ለመካብና ለመጣጥፎች ክብር ለመስጠት ሲረባረብ ይታል፡፡ በኢትዮጵያውን ህብረተሰብ ውስጥ ለመጽህፍና ለጸሐፊዎች እውቅና የሚሰጠው ሰው እጅግ ጥቂት በመሆኑ
አንዳንድ ግለሰቦች መጽሐፍና መጣጥፎችን እንዲገዙ ሲጠየቁ የደራሲውን ወይም የአዘጋጆችን ሞራል ለመጠበቅና ለማበረታታት ነው እንጂ አላነበውም እያሉ ይገዛሉ፡፡ ይህ የሚያመለክተው ለመጽሕፍት ደራሲዎችም ሆነ በየወቅቱ ጽሁፍ እያዘጋጁ ለሕዝብ ለሚያቀርቡ ግለሰቦች የተሰጠው ትኩረት መቀዝቀዙን አስተዋጸዎ ያደረጉት ምክንቶች እንዳሉ ነው፡፡
ከእነኝህም መካከል ጥቂቱ የጊዜ እጥረት፤ የኑሮ ውጥረት፤የሥራ ብዛት፤ የማንበብ ፍላጎት ማነስና ላልጠቀምበት ለምን ለመጽሐፍ ግዢ ገንዘብ አወጣለሁ የሚሉት ናቸው፡፡ ይሁንና በእውነት ህብረተሰቡ ጊዜ አጥቶ ነው እንዳይባል ትርፍ ጊዜውን አልባሌ ቦታ ሲያውለው ይታያል፡፡ የገንዘብ ችግር ስለገጠመው ነው እንዳይባል በነጻ የሚሠራጩትን መጽሄቶች እንኳን የሚያነብ ህብረተሰብ ቁጥር ውስን ነው፡፡ ታዲያ የኛ ሰው የማንበብ ዝንባሌ የለውም እየተባለ የሚነገረውን ዘልማድ ማባባስና ጸረ-ንባብ አቋማችን የሚታረመው መቼ ይሆን? መጽሐፍ የብሄራዊ ሃብት ስለሆነ የአንድ አገር ህዝብ የማንበብና የመጸፍ መብት ኖሮት ስለአገሩ ታሪክና ሰለዓለም ወቅታዊ ሁኔታ እያነበበ መረዳት የውዴታ ግዴታው ስለሆነ የአገር አስተዳዳሪዎች መሃይሙን በራዲዮና በቴሌቪዥን ዜናውን በአጭሩ እንዲያውቅ ማድረግ የብሔራዊ ግዴታቸው ነው፡፡
ይሁን እንጂ በጽሑፍ የሚሠራጩት ጽሑፎች አንብቦ እንደሚረዳው ህብረተሰብ ያህል እውቀቱን አይዳብርም፡፡ የማንበብና የመጸፍ ችሎታ ያለው ህብረተሰብ ደግሞ ከመጣጥፎች ስለጉዳዩ ይበልጥ እንዲረዳ ይገፋፋሉ፡፡ ካለበለዚያ ህዝቡ ለትምህርት ዋጋ አይሰጠውም፤ ጸሐፊ ከሌለ የአገርና የህዝብ ታሪክ አይኖርም፤ አገር ያለ ዝክረ-ታሪክ የአገርነት ምስክር አይኖራትም፡፡ ግለሰቦች መጽሐፍ የሚያነብቡት ለመዝናናት፤ አአምሮውን እያሰራ ከጨንቀትና ከድብርት በሸታ ለመራቅ፤ ታሪክን ለመረዳት፤ ጥናት ለማካሄድና አንድ ነገር ለማከናውን ሲሆን፤ እውቀትም ሆነ ጥቅም የሚገኘበት ማንኛውንም ነገር ለማግኘት በትእግስት ካላላፉ እቅድን ለመጎናጸፍ ያለመቻሉ ስለሚታወቅ ትምህርት ቤቶች ስለመጽሐፍ ጥቅም ለተማሪዎቻቸው ለማስጨበጥ በመርሃ ግብር ውስጥ እንዲታቀፍ ተደርጓል፡፡
በዚህ ምክንያት አስተማሪዎች ተማሪዎቻቸውን ወደ መጽሕፍት ቤትና የመጽሃፍ ሸያጭና ትእይንት በሚካሄድባቸው ስፍራ እየወሰዱ የሚያሰጎብኟቸው፤ የቤት ሥራቸውን መጽሐፍ እያነበቡ እንዲሠሩ የሚገፏፏቸው ዓለም ካለመጽሐፍ ህልውና እንደማይኖራት፤ የደራሲዎች የመጻፍ ጥበባቸውን ለማስገንዘብ፤ ደራሲዎችን ለማነቃቃት፤ ለመጽሐፍትና በወረቀት ላይ ለሚሰፍሩ ጽሁፎች ዋጋ ለማስጠት፤ እውቀታቸው እንዲዳብር ስለሚረዳ፤ ለመጽሕፍትና ለወቅታዊ መረጃ አሰራጮች እውቅና እንዲሰጡና የማንበብ ፍቅር እንዲያድርባቸው ወይም በአእምሮአቸው እንዲቀረጽ ለማድርግ ነው፡፡ ነገር ግን አብዛኛው ወጣቱ ትውልድ መጽሐፍትን ካለመሰልቸት እያነበበ ፈተና አልፎ ተመረቆ ከት/ቤት ከወጣ በኋላ በቴክኖሎጂው ላይ ከማተኮር በቀር በአሁኑ ጊዜ መጽሕፍትና መጣጥፎች ሲያነብ አይታይም፡፡ ይህ ደግሞ በትምህርት ቤት የቀሰመውን እውቀት ያዳክመዋል፡፡ ከትምህርት ቤት የሚቀስመው እውቀት ውስን ሆኖ ይቀራል፡፡የላቀ እውቀት እንዲኖረው አይረዳም፤ ብሎም የተማረውን እየረሳው እንዲሄዱ ስለሚያደርግ መጽሐፍት፤መጽሄቶችንና ጋዜጦችን የማንበብ ልምድ ልጆቻቸው እንዲያዳብሩ ወላጆች ቀደምት ሚና መጫወት ይኖርባቸዋል፡፡
የቴክኖሎጂ መስፋፋት መጽሐፍን ይተካዋል ወይም መጽሐፍ እያነበብኩኝ የማጠፋውን ጊዜ በአጭሩ ከኢንተርኔት አገኘዋለሁ እያሉ የሚያስቡ ግለሰቦች ካሉ ራስን እንደመደለል ነው፡፡ በእነዚህ አማካይነት የሚተላለፉ መረጃዎች ትክክለኛነታቸው ከብዙ አቅጣጫ ምንጫቸው ካልተረጋጋጠ በቀር በኢንተርኔት አማካይነት በሚያገኙት መረጃ ላይ ተመክቶ አገልግሎት ላይ ማዋል ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ ያመዝናል፡፡ በእርግጥ በኢንተርኔት ላይ የሚወጡ ጽሑፎችን በማንበብ ጠቃሚ መረጃዎች አይገኙበትም ማለት ሳይሆን አንባቢያን የሚያነብቡትን መምረጥ ይኖርባቸዋል ለማለት ነው፡፡ ከአነበቡም በኋላ ከጽሑፍ ምን ቀሰምኩኝ፡ምንስ አዲስ ነገር አገኘሁበት፡ ለእውቀቴ ምን አሰተዋጽዎ አደረገልኝ፤ ለማህበራዊ ኑሮ፤ ለሃይማኖትና ለፖለቲካ ጉዳይ ጠቃሚነቱስ እስከምን ድረሰ ነው፤ ሌላው ወገን እንዲያነበው ምክር ልሰጥ ይገባልን ብሎ ራስን መገምገም ያስፈልጋል፡፡
ይህ እንዳለ ሆኖ በወረቀት ላይ እየታተሙ በሚወጡ ጽሑፎች አማካይነት የሚገኙትን ምንጮች የሚተካ ነገር የለም፡፡ ይህም በመሆኑ የመጸሐፋ ጥቅምና ተፈላጊነት እስካሁን እንደተጠበቀ ነው፡፡ ምክንያቱም ከኮምፕይተር ተቀድተው ለአንባቢያን የሚቀርቡት አንዳንድ (ኢ-ቡክና ሌሎች ጽሁፋ-ጽሑፎች) ከቦታ ጥበት፤ ወጪን ለመቀነስና ጊዜን ለመቆጥብ ሲባል የመጸሐፍት፤ የመጽሄቶችንና የጋዜጠኞችን ያህል ሙሉ መረጃዎችን አቅፈው እንዲወጡ ስለማይደረጉ ነው፡፡ ቀደም ሲል የማንበብ ፍላጎቱና ልምድ ያዳበረ ኢትዮጵያውያን አንባቢ ህብረተሰብ በመሆኑ ከዓለም ዙሪያ ብዛት ያለው መጽሐፍ ወደ አገር ውስጥ ይገባ ነበር፡፡ አሁን ግን በኢትዮጵያውያን እየተጻፉ ከውጭ ወደ አገር ውስጥ የሚገቡና በአገር ውስጥ እየታተሙ ለሕዝብ የሚቀርቡ መጽሐፍቶችና ጽሑፋ-ጽሑፎች ብዛት ቁጥር ጨምሮ ሲታይ የአንባቢዎች ቁጥር በእጅጉ ቀንሶ የሚታይበት ምክንያት የመግዛት አቅም ስላነሳው ነው፡፡
ይህም ሆኖ የማንበብ ፍቅር ያደረበት ህብረተስብ የእለቱን ጋዜጦችና መጽሔቶች በጋራ እየተከራየ በእየአደባባዩ ተሰብስቦ ሲያነብብ ይታያል፡፡ በትምህርት የገፋውም ሆነ
ያልገፋው የማንበብ ችሎታ ያዳበረ ህብረተሰብ ሁሉ መጽሐፍ ማንበብ እንደሚገባ ህብረተሰቡን መገፋፋትና ለወጣቱ ትውልድ ምሳሌ ሆኖ መታየት ይኖርበታል እንጂ እንደ አሁኑ ጊዜ ተዳክሞ መታየቱ ምክንያቱ ምን ይሆን? ዘመን አመጣሸ ቴክኖሎጂና መሃይምነት ዓለምን መጸሐፍ አልባ ሊያድርጋት ይችላልን? ሕብረተሰቡ የመጽሐፍ ማንበብ ልምድ እንዲኖረው ምን መደረግ ይኖርበታል? ሊሚሉት ጥያቄዎች መልስ ለማግኘት ሁላችንም መጣር ይኖርብል፡፡
አንባቢያን ህብረተሰብ በበዛበት አገር፤ በወረቀትና በኤሌክትሮኒክስ አማካይነት ተዘጋጅተው የሚቀርቡ ጽሑፎች እንደልብ በሚገኙበትና ብዙ ምርጫ ባለበት አካባቢ የመኖር እድል አግኝተን ስንኖር የተጣበበ ጊዜያችንን በአግባቡ በመጠቀም መጻሕፍት፤ ጋዜጣና መጽሄቶችን በማንበብ የእውቀት አድማሳችንን በማስፋትና ራሳችንን ከአካባቢው ሰው ጋር አሰተካከሎ መገኘት አለብን እንጂ እድሉን ባለመጠቀም ኋላ ቀር ህብተሰብ ሆነን መታየት ያለብን አይመስለኝም፡፡ ቁንጽል በሆኑ የዜና ምንጮች ላይ ሳንወሰን ለማንበብ ፍላጎት ባለን ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ ጽሁፎችን እያማረጡ መመልከቱ ጠቃሚነቱ አያነጋግርም፡፡ ስለሆነም መጽሐፍት፤ በጥናት እየተደገፉ የሚወጡትን መጽሄቶችና በየቀኑ እየታተሙ ለሕዝብ የሚቀርቡትን ጋዜጦች ከማንበብ አነሰም በዛ ጠቃሚ ሃሳብና እውቀት ሰለሚገኝበት የማንበብ ባህልን ለማዳበር ያለንን ውስን ጊዜ በመጠቀም ከትምህርት ደረጃችን ጋር የሚመጥኑ ጽሑፎችን በመምረጥ ከማንበብ መቆጥብ አይኖርብንም፡፡
ደራሲውን በ(Kbdeh@yahoo.com)
No comments:
Post a Comment