Thursday, 2 November 2017

ስለ ንባብ የተለያዩ ንግርቶች


ስለ ንባብ የተለያዩ ንግርቶች፦ በህትመትም ሆነ በኤሌክትሮኒክስ ሚድያ ላይ የተጻፉ ስለንባብ የተነገሩ ንግርቶችን ማለትም ንግግሮችን የሚጻፍበት አምድ ነው፡፡


“ወረቀት መልካም እርሻ ነው፤ ብዙ ነገር ይዘራልና፡፡”- አለቃ ዘነብ ኢትዮጵያዊ“በውስጤ ያሉትን ጥሩ ነገሮች ያገኘሁት ከመጻሕፍት ነው፡፡ በሳይንስ ወይም በቀለም ሰዎች የተጻፉ መጻሕፍትን ካላነበብን የሰውን ምንነት ለማወቅ በማንችልበት ዓለም ውስጥ ነው የምንኖረው፡፡” - ማክሲም ጎርኪ“ከተጻፉት ሁሉ እርሱ በደሙ የጻፈውን እወዳለሁ፡፡ በደማችሁ ጻፉ ደም መንፈስ መሆኑን ትረዳላችሁና፡፡ በደም የሚጽፍ መነበብን አይሻም በልብ ጽላት ላይ መጻፍን እንጂ፡፡” - ፍሬደሪክ ኒቼ
“ማንበብና መተንፈስ አንድ ናቸው፡፡ ሁለቱም በትዕዛዝ አይተገበሩም አይስተጓጎሉም፡፡ ሰውን ተንፍስ ብለህ አትምከረው በሕገ ልቡናው የተጻፈ ዕውቀት ነውና፡፡ እንዲተነፍስ ግን አድርገው፡፡ ንባብም እንደዛው ነው፡፡ ሰውን አንብብ ብለህ አትምከረው እንዲያነብ ግን አድርገው፡፡ መተንፈስ ያቆምክ ዕለት ትሞታለህ ማንበብ ያቆምክ ዕለት ትወርዳለህ! የትንፋሽ ጌታ ፈጣሪ ነው፡፡ የንባብ ጌታ ደራሲ፡፡ ፈጣሪ ደራሲ ነው፡፡ ደራሲም ፈጣሪ፡፡” -  እሱባለው

 

No comments:

Post a Comment