Thursday, 2 November 2017

ንባብ በሚድያ

ንባብ በሚድያ፦ ስለ መጽሐፍ ንባብ በድምጽም ሆነ በምስል ተቀርጸው የተለቀቁ መረጃዎችን የሚለቀቅበት አምድ ነው፡፡


አንባቢ ትውልድ ለመፍጠር ምን ተደረገ?
‹‹ማንበብ ሙሉ ሰው ያደርጋል›› ቀድሞ የተነበበ ጽሑፍ በድጋሚ ተወስዶ የተለጠፈ ነው፡፡
Written by  ብርሃኑ ሰሙ
አጤ ምኒልክበሚል ርዕስ በጳውሎስ ኞኞ በተዘጋጀው መጽሐፍ ውስጥ እንደተጠቆመው፤ 1889 . የጽሕፈት ማተሚያ ማሽን ወደ ኢትዮጵያ በማስገባት የፈረንሳይ ዜግነት የነበረው ነጋዴ ቀዳሚ ቢሆንም በተለያዩ ምክንያቶች ማሽኑ አገልግሎት መስጠት አልቻለም ነበር፡፡ በ1898 . ግን ኢዲልቢ የሚባል ሶርያዊ ነጋዴ፤ የጽሕፈት ማሽን ወደ አዲስ አበባ አስመጥቶ የሕትመት ሥራ ጀማሪ ለመሆን ችሏል፡፡ የሕትመት ዘርፍ እንዲጀመርና ለዕድገቱም የውጭ አገር ዜጎች ብቻ ሳይሆኑ በተለያዩ ዘመናት የነበሩ መንግስታት፣ የሃይማኖት ተቋማትና ድርጅቶች ቀላል የማይባል አስተዋጽኦ ማድረጋቸውን መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡
ሶርያዊው ኢዲልቢ ፈረንሳዊው ነጋዴ ሞክሮ ወደ አልተሳካለት የሕትመት ዘርፍ ሲገባ ዓላማውን ከግብ ያደረሰው አፄ ምኒልክ ባደረጉለት ትብብር እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ከግዕዝ በተሻለ በአማርኛ ቋንቋ የታተሙ መፃሕፍት ቁጥር እንዲበረክቱ ሚሲዮናውያን ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከታቸው ይነገርላቸዋል፡፡ አብዛኛው የአገሪቱ ሕዝብ ለንግግር በሚጠቀምበት አማርኛ ቋንቋ የሃይማኖት መፃሕፍትን በብዛት ማተም ዓላማቸውን እንደሚያሳካላቸው የተረዱ ሚሲዮናዊያን፤ ለአገራችን የሕትመት ኢንዱስትሪ ዕድገት ቀላል የማይባል አስተዋጽኦ አድርገዋል፡፡ 
በአገራችን የመጀመሪያው ጋዜጣ እንደሆነ የሚነገርለትአዕምሮጋዜጣ ይታተምበት የነበረው መርሀ ጥበብ እና 1914 . ሥራ የጀመረው ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤቶችን በማቋቋም አፄ ምኒልክና አፄ ኃይለሥላሴ በአገር ውስጥ ፈር ቀዳጆች ሲሆኑ ከውጭ ሶሪያዊው ኢዲልቢ ይጠቀሳል፡፡ የጽሕፈት መኪናን በመጠቀም መፃሕፍት በማተሙ ሥራ ብቻ ሳይሆን በአዲስ አበባ ከተማ ቀዳሚውን የመጽሐፍ መሸጫ መደብር በመክፈትም ፈር ቀዳጆቹ የውጭ አገር ዜጎች ናቸው፡፡ ፒያሳ የሚገኘውና 60 ዓመታት ያህል አገልግሎት እንደሰጠ የሚነገርለትአፍሪካዊያን የመፃሕፍት መደብርየመጀመሪያው ባለቤቶች የውጭ አገር ዜጎች ነበሩ ይባላል፡፡ በአገራችን በየዘርፉ እንደሚታየው የምሥረታ ዕድሜያቸው ረዘም ያለ ሆኖ ያስመዘገቡት ዕድገት አዝጋሚ ነው ከሚባሉት ጋር የሚመደበው የሕትመት ሥራና ተያያዥ እንቅስቃሴዎቹም አዝጋሚ ሆነዋል፡፡ “Discovering Ethiopia” በሚል ርዕስ የኢትዮጵያ ቱሪዝም ኮሚሽን 1980 . ያሳተመው መጽሐፍ፤ በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙና በተለይ ቱሪስቶች ሊጎበኙዋቸው የሚችሉ የመፃሕፍት መደብሮች ሦስት ብቻ እንደነበሩ ያመለክታል፡፡ አንደኛው አሁንሜጋበሚል የሚጠራውና ቀድሞኩራዝይባል የነበረው የመፃሕፍት መደብር ነው፡፡ ሁለተኛው ቅርንጫፎቹ በሙሉ ተዘግተው አገልግሎት መስጠት ያቆመውኢትዮጵያ መፃሕፍት መደብርሲሆን ሦስተኛው በግሪካዊያን እንደተቋቋመ የሚነገርለትአፍሪካዊያን የመፃህፍት መደብር ነው “Discovering Ethiopia” ለቱሪስቶች ለያስተዋውቅ የሞከረው፡፡ የሕትመቱ ዘርፍና ተያያዥ አገልግሎቶቹ በፍጥነት አለማደጉ መፃሕፍት፣ ደራሲና ተደራሲያን እንዳይገናኙ እንቅፋት መሆኑን በቅድሚያ የተረዱ የሚመስሉት አፄ ኃይለሥላሴ፤ ደራሲያንን ለማበረታትና የድርሰት ሥራዎች ለአንባቢያን እንዲደርሱ የመፃሕፍትን ሙሉ የማሳተሚያ ወጪ እየሸፈኑ መፃሕፍትን ለተለያዩ ትምህርት ቤቶች እንዲደርሱ ማድረጋቸው ይነገርላቸዋል፡፡ 
የግል ማተሚያ ቤቶችን ወርሶ የመንግሥት ያደረገው ደርግ፤ በዘርፉ ያለውን ችግር ለመቅረፍ ያስችላል ብሎ ካቋቋመው ኩራዝ አሳታሚ ድርጅት ጋር የመፃሕፍት መሸጫ መደብሮችን ማደራጀቱ በበጐነቱ ተጠቃሽ ነው፡፡ ደርግ ኩራዝ አሳታሚ ድርጅትን በማቋቋም ብቻ ሳይሆን ርዕዮተ ዓለሙን ለማስፋፋት በየመስሪያ ቤቱ የውይይትና የንባብ ክበብ እንዲቋቋም ማድረጉም ወደ ኋላ ላይ አሰልቺ እየሆነ ቢመጣም ጥሎ ያለፈው መልካም ነገርም ነበር፡፡ አሁን ከፓርላማ ጀምሮ፣ በየሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች፣ በተለያዩ መንግሥታዊ ተቋማት፣ በከተሞች፣ በክፍለ ከተሞች፣ በወረዳና በቀበሌ ደረጃ በርካታ ቤተ መፃሕፍት ማቋቋም የተቻለው አንድም ከደርግ ዘመን የንባብ ክበባት ተሞክሮ ተወስዶ እንደሆነ ይነገራል፡፡ ብዙም ባያተርፍ ለኪሳራ አይዳርግም የሚባለው የሕትመት ሥራ፤ በአገራችን 1983 . በኋላ እየተስፋፋ መጥቷል፡፡ እየታተሙ በመሰራጨት ላይ ያሉ መፃሕፍት ቁጥር ጨምሯል፡፡ ኢምፐርቴክ ኢትዮጵያ ቢዝነስ ሶሳይቲየብልፅግና ቁልፍ ቁጥር 5” በሚል ርዕስ 2004 . ባሳተመው መጽሐፍ ውስጥ አንድ ሰው በዚህ ርዕሰ ጉዳይ በሰጡት ምስክርነትበሚያዝያ ወር 2003 . ብቻ በአገራችን ኢትዮጵያ 89 መፃሕፍት ታትመው ለአንባቢያን ተሰራጭተዋልይላሉ፡፡
የሕትመቱ ዘርፍ እንዲህ እያደገ የመጣ ቢመስልም ዛሬም ቢሆን የሕትመት ውጤቶች ከአንባቢያን ጋር በቅጡ አልተገናኙም ማለት ይቻላል፡፡ ለዚህ አባባሌ መነሻ የሆነኝን ገጠመኝ ከማቅረቤ በፊት የደርግ መውደቅን ተከትሎ በአዲስ አበባ ብቻ ሳይሆን በክልል ከተሞች ቅርንጫፎችን መክፈት የቻሉና ቁጥራቸው ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደጉ የመጡት የግል መፃሕፍት መሸጫ መደብሮች መነሻቸው አሮጌ መፃሕፍት የመሸጥ ሥራን መተዳደሪያ ያደረጉ ሰዎች ነበሩ፡፡ ለዚህ መነሻ በመሆንም የመርካቶው አሮጌ መጽሐፍ ተራ የአንበሳውን ድርሻ ይወስዳል፡፡ አሁን በኮልፌ፣ በአውቶቢስ ተራ፣ በፒያሳ፣ በመገናኛ፣ በጊዮርጊስ፣ በለገሀር፣ በብሔራዊ ቴአትር አካባቢዎች ከምናገኛቸው መጽሐፍ ነጋዴዎችና ባለመደብሮች ጥቂት የማይባሉት ከመርካቶው አሮጌ መጽሐፍ ተራ ጋር የተያያዘ ታሪክ ያላቸው ናቸው፡፡ የመርካቶ አሮጌ መጽሐፍ ተራ ዛሬም ቢሆን በረንዳዎችን ተጠልሎ አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡ በብዙ አሰራር፣ አስተሳሰብ፣ አካሄዳችን ውስጥ አሮጌና አዲሱ፣ ባህላዊና ዘመናዊው፣ ነባሩና መጤው፣ ፈጣንና ኋላቀሩእየተቀላቀሉ የቱን መያዝ የቱን መተው፣ የቱ ጥሩ የቱ መጥፎ፣ ምኑ ጠቃሚ፣ ማንኛውም ጐጂመሆናቸውን ለመምረጥ ስንቸገር እንደምንታየው ሁሉ፤ ከሕትመት ሥራና በተያያዥ አገልግሎቶቹ ውስጥም ዕድገትና ችግሩ ተቀላቅለው ወይም ዕድገቱ ችግሩን በበቂ ሁኔታ መቅረፍ አለመቻሉ ይታያል፡፡ 
ባለፈው ሳምንት ሚያዝያ 18 ቀን 2004 . ኮልፌ በሚኘውሜሊኒየም 2 ደረጃ የመሰናዶ ትምህርት ቤት3ተኛ ጊዜ የተሰናዳ የመፃሕፍት ቀን በዓል ዝግጅት ነበር፡፡ በዕለቱ ከኢትዮጵያ  ደራሲያን ማህበር ተጋብዘው የተገኙት አቶ አፈወርቅ በቀለ፤ የትምህር ቤቱን ቤተ መፃሕፍት ከጐበኙ በኋላ ቤተመፃህፍቱ በአማርኛ መፃሕፍት ድርቅ እንደተመታ ገልፀው ነበር፡፡ ቤተ መፃህፍቱ ካሉት  3556 መፃሕፍት ውስጥ የአማርኛ መፃሕፍት ቁጥር 321 ብቻ ነው፡፡ 164 የተማሪ መርጃ፣ 157 ደግሞ የልቦለድ መፃሕፍት፡፡ በሕትመት ዘርፉ ዕድገት ካለ፤ በየወሩ 80 የሚቆጠሩ መፃሕፍት የሚታተሙ ከሆነ፤ መፃሕፍቱን ማግኘት ያለባቸው ተማሪዎች ለምን አልደረሰም? ኢትዮጵያዊያን ደራሲያንና ኢትዮጵያዊያን ተማሪዎች እንዳይገናኙ እንቅፋት የሆነባቸው ማን ነው? ምንድን ነው? የአገሪቱን ምሁራን ዕውቀት  ካገሪቱ ተማሪዎች ጋር በመፃሕፍት በኩል ለማገናኘት የሞከሩት የአፄ ኃይለሥላሴ ተግባር አርቆ ከማሰብ የመነጨ መሆኑን ምስክርነት ለመስጠት ግድ የሚለው ለዚህ ነው፡፡ በንጉሱ ዘመን የተጀመረው መፃሕፍትን ለትምህርት ቤቶች የመለገስ ተግባር እስከ ኢሕአዴግ ዘመንም ዘልቆ ታይቷል፡፡ አሁን በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ስር ለሚገኘው የስነ ጥበብ ትምህርት ቤት ፕሬዚዳንት ግርማ ወልደጊዮርጊስ 1995 . የተለያዩ መፃሕፍትን አበርክተው ነበር፡፡ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ሚዩዚክ ሜይዴይ ለተመሳሳይ ዓላማ መንቀሳቀስ መጀመሩ ይታወቃል፡፡ ከጥቂት ሳምንታት በፊትም በብሔራዊ ቴአትር በተሰናዳ ፕሮግራም፤ ለአዲስ አበባ ማረሚያ ቤት  ቤተመፃሕፍት የሚሰጡ በሺ የሚቆጠሩ መፃሕፍት ተሰባስበው ነበር፡፡ ተማሪዎች የማንበብ ባህልን እንዲያዳብሩና በእውቀትና በመረጃ እየበለፀጉ እንዲያድጉ ከተፈለገ  ተቋማት፣ ታዋቂ ግለሰቦችና ሌሎችም መፃህፍት ለት/ቤቶች ይደርሱ ዘንድ የድርሻውን ሊያበረክቱ ይገባል፡፡ ለምሳሌአለኝ የምለው ሀብት መፃሕፍቶቼ ናቸውያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ፤ ከሀብታቸው ጥቂቱን ቆንጥረው ለአንዱ ትምህርት ቤት ቢለግሱ ለብዙዎች አርአያ ሊሆኑ ሊያነሳሱ እንደሚችሉ መገመት ይቻላል፡፡