Friday, 2 November 2018

በንባብ የበለጸገ ትውልድ እንፍጠር: ሒሳዊ ንባብ

በንባብ የበለጸገ ትውልድ እንፍጠር: ሒሳዊ ንባብ: ንባብ ለምን … ንባብ ለምኔ ? Written by  በታደሰ ለገሰ ( ሀዋሳ ) ማንበብ ሙሉ ሰው ያደርጋል   ንባብ በግለሰብም ሆነ በማህበረሰብ ህይወት ውስጥ ትልቅ ስፍራ ሊኖረው የሚገባ...



ድሮ ድሮ ማንበብ ጥሩ ልማድ ነበር፡፡
ዳዊት ደስታ ማንበብ ሙሉ ሰው ያደርጋል
ድሮ ድሮ ማንበብ ጥሩ ልማድ ነበር፡፡ አሁን ደግሞ ኢንተርኔቱ ሲመጣ ማንበብ አፈር ድሜ በላች፡፡ የመረጃው ፍጥነት ሰውን ትዕግስት የለሽ ያደርጋል፡፡ ብጣቂ ብጣቂ ነገር ማንበብ እንጂ ጊዜ የሚወስድ ዳጎስ ያለ ነገር መፍራት ያስጀምራል፡፡ ለምሳሌ ትዊተር 140 ቃላት ብቻ ካልሆነ ተጨማሪ ነገር መጻፍ ይከለክላል፡፡ ያቺ 140 ቃላት አሳብን ጭምቅ፣እምቅ፣ አድርጋ መግለጽ መቻል አለባት፡፡ በ140 ቃላት የሚረካ ሰው 1000 ቃላት ማንበብ ዳገት ይሆንበታል፡፡ እየቆየ ማኀበራዊ ድረ-ገጽ ከዚህ ሁሉ በረከቱ ጋር እንዲህ ያለውን እርግማንም አብሮ ይዞ ይመጣል፡፡
ጸሀፊኤፍሬም እሸቴ
በኢትዮጵያ የሚገኙ የአንደኛ ደረጃ ተማሪዎች አያነቡም
በኢትዮጵያ የሚገኙ 80 በመቶ የመጀመርያ ሳይክል ተማሪዎች የሚጠበቅባቸውን ያህል የንባብ ክህሎት እንደሌላቸው አንድ ጥናት አመለከተ፡፡ በኢኒሺየቲቭ አፍሪካ እና በተባባሪዎቹ በአዲስ አበባ እና በ7 ክልሎች በተካሄደው በዚሁ ጥናት መሠረት 80 በመቶ የሚሆኑት የመጀመርያ ሳይክል ተማሪዎች በሚጠበቅባቸው ደረጃ የሚያነቡ አይደሉም፡፡ በዚህ ሳቢያም ከምንባቡ የሚወጡ ጥያቄዎችን መመለስ አልቻሉም፡፡
ጥናቱ ተማሪዎች በአፍ መፍቻ ቋንቋ እንደሚማሩ መደረጉ አንብበው የመረዳት ግንዛቤያቸውን ለማሳደግ ታስቦ ቢሆንም ቃላቶችን ወደራሳቸው ቋንቋ መተርጎም አለመቻላቸው ከንባብ የመረዳት ክህሎታቸውን ዝቅ አድርጎታል ይላል ጥናቱ፡፡ በሲዳማ ካሉት ጥናቱ ከተካሄደባቸው የሁለተኛና ሦስተኛ ክፍል ተማሪዎች ሁሉም ተማሪዎች በሚጠበቅባቸው ደረጃ ልክ አለማንበባቸው በጥናቱ ተመልክቶል፡፡
በአዲስ አበባና በሐረሪ ከታየው ጎላ ያለ ውጤት ውጪ በተቀሩት ክልሎች ተማሪዎች የማንበብ አቅማቸው ዝቅተኛ ደረጃ ላይ የሚገኝ ስለሆነ ነው ይላል ጥናቱ፡፡ በሲዳማ ከሚገኙ ተማሪዎች 69.2 በመቶ የማንበብ ክህሎታቸው በጣም ደካማ መሆኑንም ጥናቱ አረጋግጦል፡፡
የሦስተኛ ክፍል ተማሪ ሆነው በጭራሽ ማንበብ የማይችሉ ተማሪዎች ያሉባቸው ክልሎች ሲዳማ 54 በመቶ እና ሶማሊያ 21.4 በመቶ ናቸው፡፡ እነዚህ ተማሪዎች ለ3 ዓመታት ያህል በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው ቢማሩም ምንም ማንበብ አለመቻላቸው ጥናቱ ይፋ አድርጎል፡፡
ቀላል ምንባብን በማዘጋጀት በከንባብ የወጡን ጥያቄዎች በመመለሱ ረገድ በተደረገው ጥናት ከግማሽ በላይ የሚሆኑት ተማሪዎች ጥያቄውን ለመመለስ ይቅርና ታሪኩን እንኳን በሚገባ ለመረዳት አለመቻላቸው ታውቋል፡፡ በአዲስ አበባና ሐረሪን በመሳሰሉ ከተሞች ካሉ የ2ኛ ክፍል ተማሪዎች 1/4ኘኛ የሚሆኑት ጥያቄዎችን መመለስ አልቻሉም፡፡ ይሄው ጥናት ለትምህርት ሚኒስቴርም ሆነ ለሌሎች ባለድርሻ አካላት ቀርቦ ውይይት እንደሚደረግበት ከኢንሺየቲቭ አፍሪካ ያገኘነው መረጃ ይጠቁማል፡፡
ምንጭአዲስ ጉዳይ፡፡ቅጽ 7 ቁጥር 172 ሐምሌ 2005